Gubae

ስምህ

Semeh

ይድነቃቸው ተካ · ኢየሱስ

Semeh is an Amharic mezmur (worship song) by Yidnekachew Teka, from the album Eyesus.

ኢየሱስዬ ስልህ ይከበኛል ሰላምህ ኢየሱስዬ ስልህ ይከበኛል ሞገስህ 4x የቱም ስም ሊለመድ ይችላል      ሃይል ያለዉ ስም ሊደክም ይችላል      ጠቢቡ ስም ድንገት ሞኝ ይሆናል      ጉልበት ያለዉ ሃይሉ ይክደዋል           የማይደክም ስም የሚያረጅ           ክብሩ ማይነጥፍ እስከ ልጅ ልጅ           መንፈሱን ልኮ አብ ያከበረው           የተቀባ ስም ኢየሱሴ ነው      ስምህ ቅባት አለው ጌታ      ስምህ እሳት አለው ጌታ      ስምህ መንፈስ አለው ጌታ      ስምህ ክብር አለው ጌታ      በስምህ ሃገር ይቀየራል      በስምህ ከተማ ይድናል      በስምህ መቃብር ይከፈታል      በስምህ የሞተው ይነሳል ከሰማይ ከገናናው ክብር ድምፅ ወጣ ከአባቴ እግዚአብሔር ምወድው ያከበርኩት ልጄ ኢየሱስ ነዉ የሾምኩት ፈቅጄ      ሙሴን አይደለም ወይም ኤሊያስን      ስሙት አብ ያለው ጌታ ኢየሱስን      ፍጥረት በሙሉ ያን ስም ስምቶ      ይታዘዘዋል ክብሩን ፈርቶ ስምህ ቅባት አለው ጌታ ስምህ እሳት አለው ጌታ ስምህ መንፈስ አለው ጌታ ስምህ ክብር አለው ጌታ በስምህ ሃገር ይቀየራል በስምህ ከተማ ይድናል በስምህ መቃብር ይከፈታል በስምህ የሞተው ይነሳል ምላስ ሁሉ ይመስክራል      ጉልበት ያለው ይንበረከካል      አለቅነት ሃይላት ስልጣናት      ሁሉም ያውቀዋል የአንተን ጌትነት ጨለማ የሚሰማው ስም ኢየሱስ 2x ችግር የሚሰማው ስም ኢየሱስ 2x ተፈጥሮ የሚገዛለት ኢየሱስ 2x አጋንንት የሚሰግድለት ኢየሱስ 2x በስምህ አጋንት ይወጣል በስምህ ከሞት ይመለጣል በስምህ ታሪክ ይቀየራል በስምህ ጨለማ ይበራል ኢየሱስ 6x ኢየሱስ ኢየሱስ ክርስቶስ ኢየሱስ የተቀባው ንጉስ

Listen on Gubae

Gubae is a free app for Android: mezmur lyrics, the Bible, church events, and a player for the music on your phone.

Get it on Google Play

More songs by Yidnekachew Teka

See all 27 songs by Yidnekachew Teka