Gubae

Sew Ayresam

ዮሴፍ አያሌው · Serayien Yeserahelegn

ዘማሪ ፡ ዮሴፍ ፡ አያሌው ርዕስ ፡ ሰው ፡ አይረሳም አልበም ፡ ሥራዬን ፡ የሠራህልኝ አዝ ሰው ፡ አይረሳም ፡ ጌታ ሰው ፡ አይረሳም ፡ ኢየሱስ (፪x) እንደ ፡ ሰው ፡ አይደለም ፡ ጌታ እንደ ፡ ሰው ፡ አይደለም ፡ ኢየሱስ (፪x) ፍቅሩ ፡ አይቀዘቅዝ ፡ ወረት ፡ አያውቀው እንደ ፡ ጌታ ፡ ያለ ፡ የትም ፡ አይገኝም የተናገረውን ፡ ቃሉ ፡ ይፈጽማል ተናግሮ ፡ ማድረግ ፡ እርሱ ፡ ብቻ ፡ ያውቃል አዝ ሰው ፡ አይረሳም ፡ ጌታ ሰው ፡ አይረሳም ፡ ኢየሱስ (፪x) እንደ ፡ ሰው ፡ አይደለም ፡ ጌታ እንደ ፡ ሰው ፡ አይደለም ፡ ኢየሱስ (፪x) ማክበርና ፡ ማንሳት ፡ ጌታ ፡ ያውቅበታል እርሱን ፡ የተጠጋ ፡ የቱ ፡ መሽቶበታል እንደ ፡ ንጋት ፡ ብርሃን ፡ ክብሩ ፡ እየጨመረ አቀማጥሎ ፡ ያኖራል ፡ እንዲህ ፡ እያከበረ አዝ ሰው ፡ አይረሳም ፡ ጌታ ሰው ፡ አይረሳም ፡ ኢየሱስ (፪x) እንደ ፡ ሰው ፡ አይደለም ፡ ጌታ እንደ ፡ ሰው ፡ አይደለም ፡ ኢየሱስ (፪x) የቱነው ፡ የተረሳ ፡ ማነው ፡ የሚጸጸት ሳይታሰብ ፡ ኖሮ ፡ ጊዜው ፡ ያለፈበት የተጣለው ፡ ይልቅ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ አድርጐ ደስታ ፡ ይሰጠዋል ፡ እንባን ፡ ከዓይኑ ፡ ጠርጐ አዝ ሰው ፡ አይረሳም ፡ ጌታ ሰው ፡ አይረሳም ፡ ኢየሱስ (፪x) እንደ ፡ ሰው ፡ አይደለም ፡ ጌታ እንደ ፡ ሰው ፡ አይደለም ፡ ኢየሱስ (፪x) አይጠረጠርም ፡ ይታመናል ፡ እንጂ እንኳን ፡ ቤቱ ፡ ኖሮ ፡ አድጐ ፡ በእርሱ ፡ እጂ ያሳልፍለታል ፡ ዘመኑን ፡ በተድላ እርዳኝ ፡ ብሎ ፡ መጥቶ ፡ የቱ ፡ ሰው ፡ ተጐዳ አዝ ሰው ፡ አይረሳም ፡ ጌታ ሰው ፡ አይረሳም ፡ ኢየሱስ (፪x) እንደ ፡ ሰው ፡ አይደለም ፡ ጌታ እንደ ፡ ሰው ፡ አይደለም ፡ ኢየሱስ (፪x)

ዮሴፍ አያሌው · ሁሉም ዘማሪዎች