Anten Keyaze Sew
ዮሴፍ አያሌው · Serayien Yeserahelegn
አዝ አንተን ፡ ከአገኘ ፡ ሰው ፡ ምን ፡ ይሆናል ፡ አሃሃ (2x) አንተን ፡ ከያዘ ፡ ሰው ፡ ምን ፡ ይሆናል ፡ አሃሃ (2x) የልቤ ፡ ማረፊያ ፡ ነህ ፡ የማምለጫ ፡ አለቴ እኮራብሃለሁኝ ፡ ኢየሱስ ፡ መድሃኒቴ (2x) አባትስ ፡ ማለት ፡ እንደ ፡ አንተ ፡ ነው ወዳጅስ ፡ ማለት ፡ እንደ ፡ አንተ ፡ ነው አሳድገኽኛል ፡ ከእጅህ ፡ እየበላሁ ሰው ፡ የሆንኩት ፡ በአንተ ፡ ነው ይህንን ፡ ልቤ ፡ አልረሳው (4x) አዝ አንተን ፡ ከአገኘ ፡ ሰው ፡ ምን ፡ ይሆናል (2x) አንተን ፡ ከያዘ ፡ ሰው ፡ ምን ፡ ይሆናል (2x) የልቤ ፡ ማረፊያ ፡ ነህ ፡ የማምለጫ ፡ አለቴ እኮራብሃለሁኝ ፡ ኢየሱስ ፡ መድሃኒቴ (2x) ዘመን ፡ ሲከፋ ፡ ሲቀያየር አንተ ፡ ግን ፡ ያው ፡ ነህ ፡ እግዚአብሔር ፀጋህ ፡ አልጐደለ ፡ ለእኔ ፡ ለልጅህ ቤትህ ፡ ያገባኛል ፡ አባብሎ ፡ ምህረትህ (4x) አዝ አንተን ፡ ከአገኘ ፡ ሰው ፡ ምን ፡ ይሆናል ፡ አሃሃ (2x) አንተን ፡ ከያዘ ፡ ሰው ፡ ምን ፡ ይሆናል ፡ አሃሃ (2x) የልቤ ፡ ማረፊያ ፡ ነህ ፡ የማምለጫ ፡ አለቴ እኮራብሃለሁኝ ፡ ኢየሱስ ፡ መድሃኒቴ (2x) አትለዋወጥ ፡ ጠዋት ፡ ማታ ፊትህ ፡ አይጠቁር ፡ የእኔ ፡ ጌታ አልቆረቆረኝም ፡ ትከሻህ ፡ ጌታዬ ተመችተኽኛል ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ አለኝታዬ (4x) አዝ አንተን ፡ ከአገኘ ፡ ሰው ፡ ምን ፡ ይሆናል ፡ አሃሃ (2x) አንተን ፡ ከያዘ ፡ ሰው ፡ ምን ፡ ይሆናል ፡ አሃሃ (2x) የልቤ ፡ ማረፊያ ፡ ነህ ፡ የማምለጫ ፡ አለቴ እኮራብሃለሁኝ ፡ ኢየሱስ ፡ መድሃኒቴ (2x) ሰማይ ፡ ምድርንም ፡ ትገዛለህ የፈቀድከውን ፡ ታደርጋለህ አንዳች ፡ አላጣሁም ፡ በስምህ ፡ ለምኜ ፊቴ ፡ አላፈረም ፡ እጅህን ፡ ታምኜ (4x) አዝ አንተን ፡ ከአገኘ ፡ ሰው ፡ ምን ፡ ይሆናል ፡ አሃሃ (2x) አንተን ፡ ከያዘ ፡ ሰው ፡ ምን ፡ ይሆናል ፡ አሃሃ (2x) የልቤ ፡ ማረፊያ ፡ ነህ ፡ የማምለጫ ፡ አለቴ እኮራብሃለሁኝ ፡ ኢየሱስ ፡ መድሃኒቴ (2x)

