Gubae

Yihie New Yegebagn

ዮሴፍ ካሳ · ዘመቻው

ዘማሪ ፡ ዮሴፍ ፡ ካሳ ሌላ ፡ ሥም ፡ ጆሲ ርዕስ ፡ ይሄ ፡ ነው ፡ የገባኝ አልበም ፡ ዝምታው ውሰድልኝ ፡ ዛሬ ፡ ከነፍሴ ፡ የሆነ ፡ አምልኮዬን አላገናኘውም ፡ ከሁኔታ ፡ ጋራ ፡ ዝማርዬን ተላንት ፡ አመስግኜ ፡ ዛሬን ፡ አላማህም ፡ እንዲህ ፡ ብዬ ይጨምራል ፡ እንጂ ፡ አላሳንሰውም ፡ ምስጋናዬ የማየው ፡ ነገር ፡ ከምስጋናዬ ፡ አያግደኝም የምሰማው ፡ አንተን ፡ ከማምለክ ፡ አያስቆመኝም ምድረበዳዬን ፡ አለምልሞታል ፡ እያየ ፡ አይኔ በህሩን ፡ ከፍሎ ፡ ያሻግረኛል ፡ አምናለሁ ፡ እኔ አዝ ይሄ ፡ ነው ፡ የገባኝ ፡ ዝም ፡ ብሎ ፡ መዘመር ሁኔታው ፡ እያለ ፡ እግዚአብሔርን ፡ ማክበር (፪x) የለመንኩትን ፡ የጠየኩትን ፡ ጥያቄ ፡ ሁሉ ከምስጋና ፡ ጋር ፡ እጠብቃለሁ ፡ አምኜ ፡ ቃሉን የከበደኝን ፡ ሸክሜን ፡ ሁሉ ፡ በእርሱ ፡ ላይ ፡ ጥዬ በአንዳች ፡ ነገር ፡ አልጨነቅም ፡ አለ ፡ ጌታዬ አዝ ይሄ ፡ ነው ፡ የገባኝ ፡ ዝም ፡ ብሎ ፡ መዘመር ሁኔታው ፡ እያለ ፡ እግዚአብሔርን ፡ ማክበር (፪x) ደመና ፡ የለም ፡ አይታየኝም ፡ በዓይኔ ነፋሥም ፡ የለም ፡ አይታየኝም ፡ በዓይኔ ሳላይ ፡ አምናለሁ ፡ እንዲሀ ፡ ይሆናል ባዶ ፡ ሸልቆ ፡ ውኃ ፡ ይሞላል አዝ ይሄ ፡ ነው ፡ የገባኝ ፡ ዝም ፡ ብሎ ፡ መዘመር ሁኔታው ፡ እያለ ፡ እግዚአብሔርን ፡ ማክበር (፪x) ምስክር ፡ ነኝ ፡ እኔ ፡ ምስክር ፡ ነኝ ፡ እኔ አይቻለሁኝ ፡ ሲሰራ ምስክር ፡ ነኝ ፡ እኔ ፡ ምስክር ፡ ነኝ ፡ እኔ ክንደ ፡ ብርቱ ፡ ነው ፡ ኃይለኛ ምስክር ፡ ነኝ ፡ እኔ ፡ ምስክር ፡ ነኝ ፡ እኔ ድንቅ ፡ ነው ፡ ተአምረኛ ምስክር ፡ ነኝ ፡ እኔ ፡ ምስክር ፡ ነኝ ፡ እኔ አይቻለሁኝ ፡ በዓይኔ ምስክር ፡ ነኝ ፡ እኔ ፡ ምስክር ፡ ነኝ ፡ እኔ

ዮሴፍ ካሳ · ሁሉም ዘማሪዎች