Gubae

Medehanialem

ዮሴፍ ካሳ · ተነሺና አብሪ

“ስብሐተ-እግዚአብሔር ፡ ይነግር ፡ አፉየ ፡ ኩሉ ፡ ዘስጋ ፡ ይባርክ ለሥሙ ፡ ቅዱስ ፡ ለዓለም ፡ ወለዓለመ-ዓለም” አሜን ፡ ሀሌሉያ ፡ እያሉ ቅዱስ ፡ አለ ፡ እርሱ ፡ ዘምሩ ዛሬም ፡ እርሱን ፡ የምትፈሩ አምላካችሁን ፡ አመስግኑ (፪x) ከድንግል ፡ ማርያም ፡ ከብፅህት ፡ ተወልዶ ወደ ፡ ምድር ፡ መጣ ፡ ዓለምን ፡ ሁሉ ፡ ወዶ በመስቀሉ ፡ ስራ ፡ ሁሉን ፡ ሊያስታርቅ የባርያን ፡ መልክ ፡ ይዞ ፡ ወረደ ፡ ያለም ፡ መድሐኒት የድሃደግ ፡ አባት ፡ የመበለት ፡ ዳኛ እራሱን ፡ አዋርዶ ፡ ሞተልን ፡ ስለኛ የሞትን ፡ ጣር ፡ ሁሉ ፡ አጥፍቶ ፡ ተነሳ የጥሉ ፡ ግድግዳ ፡ ፈረሰ ፡ ሲዖልን ፡ ድል ፡ ነሳ ተስፋ ፡ የለኝ ፡ ብሎ ፡ ውስጡ ፡ ባዘነዉ ሰው ፡ ለማይረዳው ፡ ልቡን ፡ ሚያልበዉ እንባውን ፡ አብሰህ ፡ አቅፈህ ፡ ምታጽናና ክብርና ፡ ሞገስ ፡ ይብዛልህ ፡ ምሥጋና በአብ ፡ ቀኝ ፡ ያለው ፡ (መድኃኒያለም) ስለ ፡ እኛ ፡ የሞተው ፡ (መድኃኒያለም) ከሞት ፡ የተነሳው ፡ (መድኃኒያለም) በክብር ፡ ያረገው ፡ አዬ ፡ (መድኃኒያለም) በዙፋኑ ፡ ያለው ፡ (መድኃኒያለም) ደግሞም ፡ የሚመጣው ፡ አዬ ፡ (መድኃኒያለም) እግዚአብሔርን ፡ አመስግኑ ቸርነቱን ፡ ተናገሩ ፡ (ቸር ፡ ነውና ፡ ምህረቱ ፡ ለዘላለም) ሰማያትን ፡ ሰራ ፡ (ቸር ፡ ነውና ፡ ምህረቱ ፡ ለዘላለም) ምድርን ፡ ዘረጋ ፡ (ቸር ፡ ነውና ፡ ምህረቱ ፡ ለዘላለም) መላዕክት ፡ ሰገዱ ፡ (ቸር ፡ ነውና ፡ ምህረቱ ፡ ለዘላለም) ይገባዋል ፡ አሉ ፡ (ቸር ፡ ነውና ፡ ምህረቱ ፡ ለዘላለም) ኧኸ ፡ ኧኸ ይገባዋል ፡ ይገባዋል ይገባዋል ፡ ይገባዋል ፡ (ታርዷልና) (፫x) በከበሮ ፡ (አመስግኑት) በመሰንቆ ፡ (አመስግኑት) በበገና ፡ (አመስግኑት) በዕልልታ ፡ (አመስግኑት) (፪x) ኧኸ ፡ ኧኸ ይገባዋል ፡ ይገባዋል ይገባዋል ፡ ይገባዋል ፡ (ታርዷልና) (፫x)

ዮሴፍ ካሳ · ሁሉም ዘማሪዎች