Kengedihema
ዮሴፍ ካሳ · ኑሮዬ በኪዳን ነው
ዘማሪ ፡ ዮሴፍ ፡ ካሳ ርዕስ ፡ ከእንግዲህማ አልበም ፡ ኑሮዬ ፡ በኪዳን ፡ ነው ፊቴ ፡ የቆመውን ፡ ባሕር ፡ ያኔ ፡ አሳልፎኝ ነበር ዛሬስ ፡ ደግሞ ፡ ሌላው ፡ ቢገጥመኝ ፡ በየተራ ፡ ቢሰለፍብኝ ዓይኔን ፡ ማንከራተቱን ፡ ትቼ ፡ ልምታ ፡ ከበሮዬን አንስቼ የሰልፉ ፡ ጌታ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነው ፡ ዛሬም ፡ ጠላቴን ፡ ሊያዋርደው (፪x) ያሻገረኝ ፡ ጌታ ፡ ያን ፡ የትላንቱን (፫x) አሁንም ፡ ይሰራል ፡ ያን ፡ ሃይሉን ፡ ሳምን (፫x) በእውነት ፡ ላመልከው ፡ ከልቤ ፡ ስነሳ (፫x) ሁሉን ፡ አሳመረው ፡ የይሁዳ ፡ አንበሳ (፫x) አዝ ከእንግዲህማ ፡ ወስኗል ፡ ልቤ ከእንግዲህማ ፡ ምንም ፡ ላይፈራ ከእንግዲህማ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ እያለ ፡ ከእኔ ጋራ ከእንግዲህማ ፡ ሌላውን ፡ አልሰማም ከእንግዲህማ ፡ ከንቱ ነውና ከእንግዲህማ ፡ እዘምራለው ፡ ከልቤ ፡ ለእርሱ ፡ ምሥጋና ከልቤ ፡ ለእርሱ ፡ ምሥጋና ፡ ከልቤ ፡ ለእርሱ ፡ ምሥጋና ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነውና ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነውና (፪x) ፊቴ ፡ የቆመውን ፡ ባሕር ፡ ያኔ ፡ አሳልፎኝ ፡ ነበር ዛሬስ ፡ ደግሞ ፡ ሌላው ፡ ቢገጥመኝ ፡ በየተራ ፡ ቢሰለፍብኝ ዓይኔን ፡ ማንከራተቱን ፡ ትቼ ፡ ልምታ ፡ ከበሮዬን ፡ አንስቼ የሰልፉ ፡ ጌታ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነው ፡ ዛሬም ፡ ጠላቴን ፡ ሊያዋርደው የቆመው ፡ ተራራ ፡ ፊቴ ፡ ተከምሮ (፪x) አይመስልም ፡ ሚታለፍ ፡ እንደሚከብድ ፡ ሆኖ (፪x) ለእኔ ፡ እንጂ ፡ ለአምላኬ ፡ መቼ ፡ አስቸገረው (፪x) በተአምራቱ ፡ ሁሉን ፡ ሜዳ ፡ አደረገው (፪x) አዝ ከእንግዲህማ ፡ ወስኗል ፡ ልቤ ከእንግዲህማ ፡ ምንም ፡ ላይፈራ ከእንግዲህማ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ እያለ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ከእንግዲህማ ፡ ሌላውን ፡ አልሰማም ከእንግዲህማ ፡ ከንቱ ፡ ነውና ፡ ከእንግዲህማ ፡ እዘምራለው ፡ ከልቤ ፡ ለእርሱ ፡ ምሥጋና ከልቤ ፡ ለእርሱ ፡ ምሥጋና ፡ ከልቤ ፡ ለእርሱ ፡ ምሥጋና ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነውና ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነውና (፬x)

