Egziabher Tikikil
ዮሴፍ ካሳ · Single Mezmurs
ጻድቅ ነህ በሥራህ አትሳሳትም እንዲህ አድርግ አትባልም በዚህ ዓለም ገና ምንም ሳይኖር ቅድሞም ያውቀኛል ሳልፈጠር ህይወቴን ሁሉ ያውቀዋል ጌታ ምን እንደሚሆን ምን እንዲመጣ የማይሆነውም አይሆንምና ሚሆንው ሊሆን ግድ ነውና የስንፍና ቃል ከአፌ አይወጣ ይህን ነው ምለው ጻድቅ ነው ጌታ እግዚአብሔር ትክክል (፫X) ነህ አንተ በሥራህ ጻድቅ ነህ ማን እንዲህ እንዲያ አድርግ ይልሃል ማንስ አስተያየት ይሰጥሃል ሁሉም በፈቃድህ ታደርጋለህ እግዚአብሔር አንተ ጻድቅ ነህ ጻድቅ ነህ በሥራህ አትሳሳትም እንዲህ አድርግ አትባልም የለመንኩህን የጠየቅኩህን አርግልኝ ቢዬ ሙጥኝ ያልኩህን አይሆንም ብለ ስትከለክልኝ ልቤም ሲከፋ አልገባ ሲልኝ አባት ለልጁ እንደሚራራ የሚረባኝ ታውቃለህና ይህ ነው ትክክል አንተ ያልከው ሃሳብህ ይሁን የፈቀድከው እግዚአብሔር ትክክል (፫X) ነህ አንተ በሥራህ ጻድቅ ነህ ማን እንዲህ እንዲያ አድርግ ይልሃል ማንስ አስተያየት ይሰጥሃል ሁሉም በፈቃድህ ታደርጋለህ እግዚአብሔር አንተ ጻድቅ ነህ በቃሽ ነፍሴ ሆይ ስሚኝ በእግዚአብሔር ታመኚ ሁሌ ትክክል ነው እርሱ ጻድቅ ነው ንጉሱ

