Gubae

Weletaw Bezabegn

ዮሴፍ በቀለ · ባለውለታዬ ጌታ

ዛሬ ፡ ልጅ ፡ ተብዬ ፡ ክብርን ፡ አግኝቻለሁ የቀድሞ ፡ ኑሮዬን ፡ ረስቼዋለሁ ታሪኬን ፡ ለውጠህ ፡ ሰው ፡ አድርጐ ፡ አቆመኝ የመረጥኩህ ፡ ልጄ ፡ እስራኤል ፡ ሆይ ፡ አለኝ የመረጥኩህ ፡ ልጄ ፡ የምወድህ ፡ ሆይ ፡ አለኝ አዝ ኧረ ፡ ይህን ፡ ኢየሱስ ፡ ምን ፡ ብዬ ፡ ልባርከው ውለታው ፡ በዛብኝ ፡ ከአይምሮዬም ፡ በላይ ፡ ነው አቤት ፡ ምህረቱ ፡ ምን ፡ እከፍለዋለሁ እኔም ፡ ክብር ፡ አግኝቼ ፡ አገልጋል ፡ ሆኛለሁ ይኸው ፡ ይድረስልኝ ፡ ዛሬም ፡ ምሥጋናዬ ፡ ኤሄሄ ማለት ፡ ችያለሁኝ ፡ እኔም ፡ አባብዬ (፪x) በክርስትናዬ ፡ እድሜን ፡ ቆጥሬያለሁ በልማዳዊ ፡ ሕይወት ፡ ተመላልሻለሁ ዛሬ ፡ ግን ፡ ኢየሱስ ፡ ነፍሴ ፡ አወቀችህ አምላኬ ፡ ጌታዬ ፡ ውዴ ፡ ነህ ፡ አለችህ አምላኬ ፡ ጌታዬ ፡ አባቴ ፡ አለችህ አዝ ኧረ ፡ ይህን ፡ ኢየሱስ ፡ ምን ፡ ብዬ ፡ ልባርከው ውለታው ፡ በዛብኝ ፡ ከአይምሮዬም ፡ በላይ ፡ ነው አቤት ፡ ምህረቱ ፡ ምን ፡ እከፍለዋለሁ እኔም ፡ ክብር ፡ አግኝቼ ፡ አገልጋል ፡ ሆኛለሁ ይኸው ፡ እድረስልኝ ፡ ዛሬም ፡ ምሥጋናዬ ፡ ኤሄሄ ማለት ፡ ችያለሁኝ ፡ እኔም ፡ አባብዬ (፪x) የስጋዬን ፡ ሳስብ ፡ እንዲያው ፡ ስቅበዘበዝ ጠላት ፡ ቤቴ ፡ ገብቶ ፡ ምርኮን ፡ ሲበዘብዝ እርሱ ፡ ግን ፡ ጌታዬ ፡ አሰበኝ ፡ ለአንድ ፡ አፍታ ኃይሌም ፡ ተመለሰ ፡ ጠላቴም ፡ ተረታ ኃይሌም ፡ ተመለሰ ፡ ይክበር ፡ የእኔ ፡ ጌታ አዝ ኧረ ፡ ይህን ፡ ኢየሱስ ፡ ምን ፡ ብዬ ፡ ልባርከው ውለታው ፡ በዛብኝ ፡ ከአይምሮዬም ፡ በላይ ፡ ነው አቤት ፡ ምህረቱ ፡ ምን ፡ እከፍለዋለሁ እኔም ፡ ክብር ፡ አግኝቼ ፡ አገልጋል ፡ ሆኛለሁ ይኸው ፡ እድረስልኝ ፡ ዛሬም ፡ ምሥጋናዬ ፡ ኤሄሄ ማለት ፡ ችያለሁኝ ፡ እኔም ፡ አባብዬ

ዮሴፍ በቀለ · ሁሉም ዘማሪዎች