Mesqeleh Ser
ዮሴፍ በቀለ · ባለውለታዬ ጌታ
እናንተ ፡ ደካሞች ፡ ሸክም ፡ የከበዳችሁ ፡ ሁሉ ወደ ፡ እኔ ፡ ኑ ፡ እኔም ፡ አሳርፋቹሃለሁ የማቴዎስ 11:28 ዘማሪ ፡ ዮሴፍ ፡ በቀለ ርዕስ ፡ መስቀልህ ፡ ስር አልበም ፡ ባለውለታዬ ፡ ጌታ አዝ እስኪ ፡ መስቀልህ ፡ ስር ፡ ሸክሜን ፡ ልጣለው (፪x) ኦሆ ፡ ኦሆ ማረፊያዬ ፡ ኢየሱስ ፡ ሰላሜ ፡ በአንተ ፡ ነው ፡ እረፍቴ ፡ በአንተ ፡ ነው ፡ አዎ ሁሉ ፡ ያለቀበትን ፡ መስቀልክን ፡ እያየሁ (፪x) ኦሆ ፡ ኦሆ ያኔ ፡ መከራዬን ፡ ችግሬን ፡ እረሳለሁ ፡ ጭንቀቴን ፡ እረሳለሁ ፡ አዎ ክላሲካል በቀራኒዮ ፡ ላይ ፡ ስለእኔ ፡ ተሰቅለህ (፪x) ኦሆ ፡ ኦሆ አንተ ፡ በእኔ ፡ ፈንታ ፡ እርጉም ፡ ሰው ፡ ተብለህ (፪x) አዎ ተፈጸመ ፡ ብለህ ፡ ሁሉንም ፡ ጨረስከው (፪x) ኦሆ ለዘለዓለሙ ፡ መርገሜን ፡ ወሰድከው ፡ እዳዬን ፡ ከፈልከው ፡ አዎ መራራውን ፡ ጽዋ ፡ ጠጣህ ፡ በእኔ ፡ ፈንታ የታሰርኩበትም ፡ ሰንሰለት ፡ ተፈታ መስቀልህ ፡ ስር ፡ አለሁ ፡ ጥያቄዬን ፡ ይዤ ከላዬ ፡ ውሰደው ፡ ኢየሱስ ፡ ወዳጄ ክላሲካል አዝ እስኪ ፡ መስቀልህ ፡ ስር ፡ ሸክሜን ፡ ልጣለው (፪x) አዎ ማረፊያዬ ፡ ኢየሱስ ፡ ሰላሜ ፡ በአንተ ፡ ነው ፡ እረፍቴ ፡ በአንተ ፡ ነው ፡ አዎ ሁሉ ፡ ያለቀበትን ፡ መስቀልክን ፡ እያየሁ (፪x) ኦሆ ፡ ኦሆ ያኔ ፡ መከራዬን ፡ ችግሬን ፡ እረሳለሁ ፡ ጭንቀቴን ፡ እረሳለሁ ፡ አዎ ክላሲካል ሸክም ፡ ሲያንገላታኝ ፡ ቀንበር ፡ ሲከብድብኝ (፪x) ኦሆ ፡ ኦሆ ጨለማው ፡ በርትቶ ፡ መሄጃው ፡ ሲጠፋኝ (፪x) አዎ ቀና ፡ ብዬ ፡ ሳይህ ፡ ስጠራህ ፡ ጌታዬ (፪x) ኦሆ ፡ ኦሆ ፈጥነህ ፡ ድረስና ፡ ስበርው ፡ ከላዬ ፡ ቀንበሩን ፡ ከላዬ ፡ አዎ ከእናት ፡ ከአባት ፡ በላይ ፡ ቀርበህ ፡ ምትረዳኝ ሚስጢሬን ፡ ተካፋይ ፡ ማን ፡ እንደ ፡ አንተ ፡ ጌታ ገበናዬን ፡ ሸፋኝ ፡ ሚስጢረኛዬ ፡ ነህ ከማንም ፡ ከምንም ፡ ትበልጥብኛለህ ከታላቁ ፡ ስፍራ ፡ ከዛ ፡ የወረድከው ፍቅር ፡ ያስገደደህ ፡ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ለእኔ ፡ ነው (፪X) ችግሬን ፡ ሚረዳኝ ፡ እንደ ፡ አንተ ፡ የለምና ሁሉን ፡ ነግርሃለሁ ፡ ፊትህ ፡ እደፋና።

