Gubae

Mahetemien Yefetah

ዮሴፍ በቀለ · Mahetemien Yefetah

ክበር ፡ ክበር (፪x) ንገሥ ፡ ንገሥ (፪x) ክበር ፡ ክበር (፪x) ንገሥ ፡ ንገሥ (፪x) ክበር ፡ እልሃለሁ ፡ ጌታ ፡ አንተ ፡ የእኔ ፡ አለኝታ ንገሥ ፡ እልሃለሁ ፡ ኢየሱስ ፡ የሕይወቴ ፡ ንጉሥ አዝ፦ ማኅተሜን ፡ የፈታህ ፡ ቀንበሬን ፡ ሰበርከው የዕዳ ፡ ጽፈቴን ፡ በአንዴ ፡ ደመሰስከው ጨለማዬ ፡ በርቷል ፡ ነጻ ፡ ወጥቻለሁ አመሰግንሃለሁ (፬x) ክፉዬን ፡ የማትወደው ፡ ሁሌ ፡ የምትሳሳልኝ ስለእኔ ፡ የምትማልድ ፡ አባቴ ፡ እኮ ፡ አለኸኝ በቀራኖዮ ፡ ታሪክን ፡ ሰርተህ ፡ ጠላቴን ፡ አሸንፈሃል ያሰረኝ ፡ ትብታብ ፡ ተፈቶ ፡ ዛሬማ ፡ ያዘምረኛል (፪x) ዛሬ ፡ እንዲህ ፡ ያዘምረኛል ዛሬም ፡ ሃሌሉያ ፡ ነገም ፡ ሃሌሉያ ሁሌም ፡ ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ሃ ፡ ሃሌሉያ (፫x) አዝ፦ ማኅተሜን ፡ የፈታህ ፡ ቀንበሬን ፡ ሰበርከው የዕዳ ፡ ጽፈቴን ፡ በአንዴ ፡ ደመሰስከው ጨለማዬ ፡ በርቷል ፡ ነጻ ፡ ወጥቻለሁ አመሰግንሃለሁ (፬x) ጨለማ ፡ በአንተ ፡ ዘንድ ፡ የለም ብርሃን ፡ ነህ ፡ ሁሌ ፡ ምትበራ የንጋቱ ፡ ኮከብ ፡ ኢየሱስ ፡ ብርሃን ፡ ለጨለማ አንተ ፡ ስትመራኝ ፡ ረድኤቴ ፡ አረማመዴ ፡ ቀናልኝ ብሩህ ፡ ተስፋን ፡ አይቻለሁ ፡ ኢየሱስ ፡ ከፍ ፡ በልልኝ ኢየሱስ ፡ ከፍ ፡ በልልኝ ፡ አባቴ ፡ ከፍ ፡ በልልኝ ዛሬም ፡ ሃሌሉያ ፡ ነገም ፡ ሃሌሉያ ሁሌም ፡ ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ሃ ፡ ሃሌሉያ (፫x) አዝ፦ ማኅተሜን ፡ የፈታህ ፡ ቀንበሬን ፡ ሰበርከው የዕዳ ፡ ጽፈቴን ፡ በአንዴ ፡ ደመሰስከው ጨለማዬ ፡ በርቷል ፡ ነጻ ፡ ወጥቻለሁ አመሰግንሃለሁ (፬x) ፍቅርህ ፡ ከአይምሮ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ምህረትህ ፡ እጅግ ፡ የበዛ ጥሩ ፡ ነህ ፡ ለእኔስ ፡ ኢየሱስ ፡ ሆንክላት ፡ ለነፍሴ ፡ ቤዛ ብቻህን ፡ ተዐምራት ፡ ሰርተህ ፡ መንጥቀህ ፡ አውጥተኸኛል እርግማኔን ፡ አነሳኸው ፡ በረከትህ ፡ አግኝቶኛል በረከትህ ፡ አግኝቶኛል (፪x) ክበር ፡ ክበር (፪x) ንገሥ ፡ ንገሥ (፪x) ክበር ፡ ክበር (፪x) ንገሥ ፡ ንገሥ (፪x) ክበር ፡ እልሃለሁ ፡ ጌታ ፡ አንተ ፡ የእኔ ፡ አለኝታ (አ ፡ ኢየሱስ) ንገሥ ፡ እልሃለሁ ፡ ኢየሱስ ፡ የሕይወቴ ፡ ንጉሥ አዝ፦ ማኅተሜን ፡ የፈታህ ፡ ቀንበሬን ፡ ሰበርከው የዕዳ ፡ ጽፈቴን ፡ በአንዴ ፡ ደመሰስከው ጨለማዬ ፡ በርቷል ፡ ነጻ ፡ ወጥቻለሁ አመሰግንሃለሁ (፰x)

ዮሴፍ በቀለ · ሁሉም ዘማሪዎች