Gubae

Maderiyah Denq New

ዮሴፍ በቀለ · Mahetemien Yefetah

አዝ፦ የሰራዊት ፡ አምላክ ፡ ሆይ ማደሪያህ ፡ እንዴት ፡ ድንቅ ፡ ነው ማደሪያህ ፡ እንዴት ፡ ልዩ ፡ ነው ማደሪያህ ፡ የተወደደ ፡ ነው ፡ አዎ (፪x) ነፍሴ ፡ አንተን ፡ አደባባዮችህ ወደደችህ ፡ አሃሃሃ ፡ ወደደችህ ፡ አዎ (፪x) አእላፋት ፡ መላእክት ፡ በፊትህ ቅድስናህን ፡ ሚያውጁልህ ዙፋንህ ፡ ቅዱስ ፡ ነው ፡ ገናና በምሥጋናም ፡ የተፈራህ ድምጽህ ፡ እንደብዙዎች ፡ ነው ቃልህ ፡ ከማር ፡ እልቅ ፡ ጣፋጭ ፡ ነው በምክርህ ፡ ግሩም ፡ ነህ ፡ ጌታዬ ዙፋኑ ፡ የአንተ ፡ ነው ፡ የልቤ በምክርህ ፡ ግሩም ፡ ነህ ፡ ጌታዬ ዛሬም ፡ ሾሜሃለሁ ፡ በላዬ አዝ፦ የሰራዊት ፡ አምላክ ፡ ሆይ ማደሪያህ ፡ እንዴት ፡ ድንቅ ፡ ነው ማደሪያህ ፡ እንዴት ፡ ልዩ ፡ ነው ማደሪያህ ፡ የተወደደ ፡ ነው ፡ አዎ (፪x) ነፍሴ ፡ አንተን ፡ አደባባዮችህ ወደደችህ ፡ አሃሃሃ ፡ ወደደችህ ፡ አዎ (፪x) አቤቱ ፡ ውበትህ ፡ ያማረ እኔስ ፡ አላየሁም ፡ እንደአንተ ፍጥረት ፡ ተደነቀ ፡ በስራህ አቤት ፡ የእኔስ ፡ ጌታ ፡ ልዩ ፡ ነህ በትንሿ ፡ ልቤ ፡ ገብተሃል ማደሪያ ፡ ቤትህ ፡ አድርገሃል አኔም ፡ ሁልጊዜ ፡ ላምልክህ ኢየሱስ ፡ ጌታዬ ፡ ልበልህ እኔም ፡ ሁልጊዜ ፡ ላክብርህ ኢየሱስ ፡ ጌታዬ ፡ ልበልህ ኢየሱሴ ፡ ጌታዬ ፡ አምባዬ ፡ ጋሻዬ እውነተኛ ፡ ወዳጅ ፡ እንደአንተ ፡ ማነው በጨለማው ፡ ሌሊት ፡ ፈጥኖ ፡ ሚደርሰው ነፍሴ ፡ አንተን ፡ ባርኮ ፡ አጸለችም ክበር ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ለዘለዓለም (፪x) አምላኬ ፡ አሃ ፡ ያደረከው ፡ ነገር ፡ ለእኔ የሰራኸው ፡ ስራ ፡ በዘመኔ ቢነገር ፡ ቢነገር ፡ ስጦታህ መች ፡ ያልቃል ፡ ጌታዪ ፡ ደግነትህ መች ፡ ያልቃል ፡ አባትዬ ፡ ደግነትህ ባወራው ፡ ባወራው ፡ ስጦታህን መች ፡ ያልቃል ፡ ኢየሱስዬ ፡ በጐነትህ መች ፡ ያልቃል ፡ ወዳጄ ፡ በጐነትህ አዝ፦ የሰራዊት ፡ አምላክ ፡ ሆይ ማደሪያህ ፡ እንዴት ፡ ድንቅ ፡ ነው ማደሪያህ ፡ እንዴት ፡ ልዩ ፡ ነው ማደሪያህ ፡ የተወደደ ፡ ነው ፡ አዎ (፪x) ነፍሴ ፡ አንተን ፡ አደባባዮችህ ወደደችህ ፡ አሃሃሃ ፡ ወደደችህ ፡ አዎ (፪x) አእላፋት ፡ መላእክት ፡ በፊትህ ቅድስናህን ፡ ሚያውጁልህ ዙፋንህ ፡ ቅዱስ ፡ ነው ፡ ገናና በምሥጋናም ፡ የተፈራህ ድምጽህ ፡ እንደብዙዎች ፡ ነው ቃልህ ፡ ከማር ፡ እልቅ ፡ ጣፋጭ ፡ ነው በምክርህ ፡ ግሩም ፡ ነህ ፡ ጌታዬ ዙፋኑ ፡ የአንተ ፡ ነው ፡ የልቤ በምክርህ ፡ ግሩም ፡ ነህ ፡ ጌታዬ ዛሬም ፡ ሾሜሃለሁ ፡ በላዬ አዝ፦ የሰራዊት ፡ አምላክ ፡ ሆይ ማደሪያህ ፡ እንዴት ፡ ድንቅ ፡ ነው ማደሪያህ ፡ እንዴት ፡ ልዩ ፡ ነው ማደሪያህ ፡ የተወደደ ፡ ነው ፡ አዎ (፪x) ነፍሴ ፡ አንተን ፡ አደባባዮችህ ወደደችህ ፡ አሃሃሃ ፡ ወደደችህ ፡ አዎ (፪x) አቤቱ ፡ ውበትህ ፡ ያማረ እኔስ ፡ አላየሁም ፡ እንደአንተ ፍጥረት ፡ ተደነቀ ፡ በስራህ አቤት ፡ የእኔስ ፡ ጌታ ፡ ልዩ ፡ ነህ በትንሿ ፡ ልቤ ፡ ገብተሃል ማደሪያ ፡ ቤትህ ፡ አድርገሃል አኔም ፡ ሁልጊዜ ፡ ላምልክህ ኢየሱስ ፡ ጌታዬ ፡ ልበልህ እኔም ፡ ሁልጊዜ ፡ ላክብርህ ኢየሱስ ፡ ጌታዬ ፡ ልበልህ ኢየሱሴ ፡ ጌታዬ ፡ አምባዬ ፡ ጋሻዬ እውነተኛ ፡ ወዳጅ ፡ እንደአንተ ፡ ማነው በጨለማው ፡ ሌሊት ፡ ፈጥኖ ፡ ሚደርሰው ነፍሴ ፡ አንተን ፡ ባርኮ ፡ አጸለችም ክበር ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ለዘለዓለም (፪x) አምላኬ ፡ አሃ ፡ ያደረከው ፡ ነገር ፡ ለእኔ የሰራኸው ፡ ስራ ፡ በዘመኔ ቢነገር ፡ ቢነገር ፡ ስጦታህ መች ፡ ያልቃል ፡ ጌታዪ ፡ ደግነትህ መች ፡ ያልቃል ፡ አባትዬ ፡ ደግነትህ ባወራው ፡ ባወራው ፡ ስጦታህን መች ፡ ያልቃል ፡ ኢየሱስዬ ፡ በጐነትህ መች ፡ ያልቃል ፡ ወዳጄ ፡ በጐነትህ

ዮሴፍ በቀለ · ሁሉም ዘማሪዎች