Gubae

Lekber Yemihon Eqa

ዮሐንስ ግርማ · አምላኬ ደስታዬ

ጨለማ በሆነበት ብርሃንን የሚያበራ ስለ ከበረው ፀዳልህ ሚያወራ ሙት በገዛው ሸለቆ ሕይወትን የሚናገር ወደ ሞት ለሚነዱት ብርሃን የሚሆን የምሥራችን የሚያበስር ለክብርህ የሚሆን እቃ (3 ጊዜ)   አርገኝ ጌታ   አንተን የማያሳፍር   ክቡር ስምህን የሚሸከም      ሙሉ ማንነቱን ላንተ የሚሰጥ   ታማኝ ባርያ የማያሳፈር (2 ጊዜ) የወርቅ እቃ የምትለው በእሳትህ የነጠረ የምትሻውን ልታደርግበት ያማረ ሕያው ቅዱስ መስዋዕት አርጎ ራሱን የሰጠ ባለህበት አብሮ የሚኖር የማይርቅ እንዳስቀመጥከው የሚቀመጥ ለክብርህ የሚሆን እቃ . . . በዓለም ከሚታደለው ከጊዜያዊ ደስታ ሰማያዊውን ለመያዝ ልዘርጋ ዓለምን ነፍሴ ትጥላ በአይኖቼ ክብርን ትጣ በንቀት እያየኋት ላንት ልሩጥ ፍሬን ላፍራ አንትን ላኩራ ለክብርህ የሚሆን እቃ . . .

ዮሐንስ ግርማ · ሁሉም ዘማሪዎች