Kemegegneteh Wediet Ehiedalehu
ዮሐንስ ግርማ · አምላኬ ደስታዬ
ከአፈር የተነቀለ ሳር ጠውልጐ ደርቆ እንደሚታይ ልምላሜን ርቆ ከሕልውናህ ውጭ መኖር ለእኔ ይከብዳል ክፍት ክፍት እያለ ሁሌ ሆድ ያስብሳል (፪x) አዝ ከመገኘትህ ወዴት እሄዳለሁ ከህልውናህስ ምንን እመርጣለሁ ሳበኝ አስጠጋኝ ከጉያህ ሥር ዙሪያው ብርድ ነው ፈለኩ ሙቀትህን ሳበኝ አስጠጋኝ ከጉያህ ሥር ዙሪያው ብርድ ነው ፈለኩ ሙቀትህን (፪x) በእጆችህ አጥብቀህ እኔን ይዘኸኛል ይህንንም እውነት ቃልህ ይናገራል ነገሩ ከገባኝ ዕንቁ መሆንህ ለምን አንተ ብቻ እኔም ልያዝህ/ላጥብቅህ (፪x) አዝ ከመገኘትህ ወዴት እሄዳለሁ ከህልውናህስ ምንን እመርጣለሁ ሳበኝ አስጠጋኝ ከጉያህ ሥር ዙሪያው ብርድ ነው ፈለኩ ሙቀትህን ሳበኝ አስጠጋኝ ከጉያህ ሥር ዙሪያው ብርድ ነው ፈለኩ ሙቀትህን (፪x) ከአንተ እርቆ ሰው እንዴት እንደሚኖር እኔ አይገባኝም ትምክህቱ ምን ይሆን ከህልውናህ ውጭ እልፍ ከሚያጅበኝ ከመገኘትህ ውስጥ የተጣልኩ ያድርገኝ (፪x) አዝ ከመገኘትህ ፡ ወዴት ፡ እሄዳለሁ ከህልውናህስ ምንን እመርጣለሁ ሳበኝ አስጠጋኝ ከጉያህ ሥር ዙሪያው ብርድ ነው ፈለኩ ሙቀትህን ሳበኝ አስጠጋኝ ከጉያህ ሥር ዙሪያው ብርድ ነው ፈለኩ ሙቀትህን (፪x)ዠፘ

