9
ይድነቃቸው ተካ · ኢየሱስ
መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ላንተ ፡ ያለኝ ፡ ትልቅ ፡ ቦታ በምንም ፡ አልተካው ፡ የኔ ፡ እድል ፡ ፈንታ ላንተ ፡ አብሮነት ፡ ያለኝ ፡ ትልቅ ፡ ቦታ በምንም ፡ አልተካው ፡ የኔ ፡ እድል ፡ ፈንታ የግድ ፡ ታስፈልገኛለህ የግድ ፡ ታስፈልገኛለህ የግድ ፡ ታስፈልገኛለህ የምሬን ፡ ነው ፡ ታስፈልገኛለህ ሰው ፡ እንዴት ፡ ትንሽ ፡ ነው ብቻውን ፡ ከወጣ ፡ ያላንተ ቀትረ ፡ ቀላል ፡ ሆኖ ይኖራል ፡ ሁሌ ፡ እንደዋተተ ግን ፡ አብሮህ ፡ ያለ ፡ ሰው መንፈስህ ፡ ያጀበው ፡ ከኋላ ሕዝብን ፡ ይታደጋል በእየሱስ ፡ ምድርን ፡ እየሞላ በህይወቴ ፡ የነገርከኝ ያስጀመርከኝ ፡ መንገድ ብቻዬን ፡ አልደፍረውም መንፈስህ ፡ ነው ፡ የግድ በሰው ፡ አፍ ፡ ብቻ ፡ አውርቼ አይደለም ፡ የማሳምነው ወይ ፡ ከእግረኛ ፡ ጋር ፡ ሮጬ ልድረስበት ፡ የምለው መኖር ፡ አልችልም ፡ ያላንተ እኔ ፡ አለመድኩም ፡ ያላንተ አገልግሎትም ፡ ያላንተ አይሞከርም/አይደፈርም ፡ ያላንተ (፪x) የግድ ፡ ታስፈልገኛለህ የግድ ፡ ታስፈልገኛለህ የግድ ፡ ታስፈልገኛለህ የምሬን ፡ ነው ፡ ታስፈልገኛለህ አይቀልብኝ ፡ ጌታ ፡ አብሮነትህ ጌታ ፡ አብሮነትህ እኔ ፡ አልለምደውም እየሱስ ፡ አብሮነትህን ጌታ ፡ አብሮነትህን የኔ ፡ ሞገስ ፡ ክብሬ (አንተ ፡ ነህ ፡ አንተ) የኔ ፡ ማስፈራቴ (አንተ ፡ ነህ ፡ አንተ) እሩቅ ፡ የምሄድብህ (አንተ ፡ ነህ ፡ አንተ) መቼም ፡ የማልቆምብህ (አንተ ፡ ነህ ፡ አንተ) እኔ ፡ የለመድኩት (ከአንተ ፡ ጋር) የእውነት ፡ የምኖረው (ከአንተ ፡ ጋር) አገልግሎቴ (ከአንተ ፡ ጋር) መቼም ፡ የማይቆመው (ከአንተ ፡ ጋር) ሀገር ፡ የሚሰማኝ (ከአንተ ፡ ጋር) ምድርን ፡ የምወርሰው (ከአንተ ፡ ጋር) ጠላት ፡ የሚፈራኝ (ከአንተ ፡ ጋር) የማልለመደው (ከአንተ ፡ ጋር) የግድ ፡ ታስፈልገኛለህ የግድ ፡ ታስፈልገኛለህ የግድ ፡ ታስፈልገኛለህ የምሬን ፡ ነው ፡ ታስፈልገኛለህ ጣልቃ ፡ የማትገባበት ፡ የማትሳተፍበት የሕይወቴ ፡ ክፍል ፡ የለም አንተን ፡ የማያካትት እውቅና ፡ እሰጥሃለሁ ፡ በነገሬ ፡ ሁሉ ፡ ላይ ዘንግቼህ ፡ አቅም ፡ የለኝ የት ፡ ልሄድ ፡ አንተን ፡ ሳላይ

