Egziabhier Kenie Gar Bayhon Noro
ወርቅነህ አላሮ · ከእሳት ውስጥ የነጠቀኝ
እግዚአብሔር ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ባይሆን ፡ ኖሮ ፡ በእነዚህ ፡ ዓመታት በክንዱ ፡ ደግፎ ፡ ባያሻግረኝ ፡ ክፉዎቹን ፡ ቀናት አጠገቤ ፡ ቆሞ ፡ ባያበረታኝ ፡ በነውጡ ፡ ሰዓት ሕያው ፡ ሳለሁኝ ፡ በዋጠኝ ፡ ነበር ፡ ጠላቴ ፡ እንደቁጣው ፡ ጽናት (፪x) የአመጽን ፡ ፈሳሽ ፡ እያደረቀ ፡ የጥፋትን ፡ ጎርፍ ፡ እየገደበ ነፍሴን ፡ እንደወፍ ፡ ከአዳኞች ፡ ወጥመድ ፡ እያስመለጣት ላኖረኝ ፡ ጌታ ፡ እስቲ ፡ ልሰዋ ፡ የምሥጋናን ፡ መስዋዕት (ሃሌሉያ) ፡ ሃሌሉ ፡ (ሃሌሉያ) ፡ ሃሌሉ...ሃሌሉያ (ኦ ፡ ሃሌሉያ) ፡ ሃሌሉ...ሃሌሉ...ሃሌሉያ በመከራዬ ፡ ቀን ፡ ልመናዬን ፡ ሰማኝ ከላይ ፡ ከመቅደሱ ፡ ረድኤቱን ፡ ላከልኝ የጠላቶቼን ፡ ከፍታ ፡ አስረገጠኝ በማዳኑ ፡ እጅግ ፡ ደስ ፡ አሰኘኝ (፪x) (ሃሌሉያ) ፡ ሃሌሉ ፡ (ሃሌሉያ) ፡ ሃሌሉ...ሃሌሉያ (ኦ ፡ ሃሌሉያ) ፡ ሃሌሉ...ሃሌሉ...ሃሌሉያ ለጥርሱ ፡ ንክሻ ፡ አላደረገኝ ከተደበቀብኝ ፡ ወጥመድ ፡ አዳነኝ ነፍሴን ፡ ከመከራ ፡ ሁሉ ፡ ላዳናት ለጌታ ፡ ለኢየሱስ ፡ ዘሬም ፡ ይገዛለት (፪x) (ሃሌሉያ) ፡ ሃሌሉ ፡ (ሃሌሉያ) ፡ ሃሌሉ...ሃሌሉያ (ኦ ፡ ሃሌሉያ) ፡ ሃሌሉ...ሃሌሉ...ሃሌሉያ ምንም ፡ ያህል ፡ ብዙ ፡ ወዳጆች ፡ ቢኖሩም በመከራ ፡ ቀን ፡ ግን ፡ ማንም ፡ አይገኝም ፍፁም ፡ ሳይለወጥ ፡ ልመናን ፡ ሚፈጽም ታማኙ ፡ እግዚአብሔር ፡ ይክበር ፡ ለዘለዓለም ፊቱ ፡ ሳይቀየር ፡ ልመናን ፡ ሚፈጽም ታማኙ ፡ እግዚአብሔር ፡ ይክበር ፡ ለዘለዓለም (ሃሌሉያ) ሃሌሉ (ሃሌሉያ) ፡ ሃሌሉ...ሃሌሉያ (ኦ ፡ ሃሌሉያ) ፡ ሃሌሉ...ሃሌሉ...ሃሌሉያ የተግሳጽና ፡ የዘለፋው ፡ ብዛት አቤት ፡ በመከራ ፡ ቀን ፡ የተግዳሮት ፡ አይነት የጠላትን ፡ ትዕቢት ፡ የጨለማውን ፡ ብርታት በአንዲት/በአፉ ፡ ቃል ፡ ሽሮ ፡ ያከብራል ፡ በቅጽበት (፪x) እግዚአብሔር ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ባይሆን ፡ ኖሮ ፡ በእነዚህ ፡ ዓመታት በክንዱ ፡ ደግፎ ፡ ባያሻግረኝ ፡ ክፉዎቹን ፡ ቀናት አጠገቤ ፡ ቆሞ ፡ ባያበረታኝ ፡ በነዉጡ ፡ ሰዓት ሕያው ፡ ሳለሁኝ ፡ በዋጠኝ ፡ ነበር ፡ ጠላቴ ፡ እንደቁጣው ፡ ጽናት (፪x) የአመጽን ፡ ፈሳሽ ፡ እያደረቀ ፡ የጥፋትን ፡ ጎርፍ ፡ እየገደበ ነፍሴን ፡ እንደወፍ ፡ ከአዳኞች ፡ ወጥመድ ፡ እያስመለጣት ላኖረኝ ፡ ጌታ ፡ እስቲ ፡ ልሰዋ ፡ የምሥጋናን ፡ መስዋዕት (ሃሌሉያ) ፡ ሃሌሉ ፡ (ሃሌሉያ) ፡ ሃሌሉ...ሃሌሉያ (ኦ ፡ ሃሌሉያ) ፡ ሃሌሉ...ሃሌሉ...ሃሌሉያ

