ዘመኑ ፈጠነ
Zemenu Fetene
ተስፋዬ ጋቢሶ · ክርስቲያን ተሻገረ
ዘማሪ ፡ ተስፋዬ ጋቢሶ ርዕስ ፡ ዘመኑ ፡ ፈጠነ አልበም ፡ ክርስቲያን ፡ ተሻገረ አዝ ዘመኑ ፡ ፈጠነ ፡ ሮጠ ፡ ገሰገሰ የጌታችን ፡ መምጫ ፡ ጊዜያቱ ፡ ደረሰ ሰዎች ፡ ቶሎ ፡ በሉ ፡ መከሩን ፡ ሰብስቡ የተጣለብንን ፡ አደራ ፡ አስቡ ሰዓቱ ፡ ሊሞላ ፡ በቅርብ ፡ ነው ፡ ያለው መለከት ፡ ሊነፋ ፡ በቅርብ ፡ ነው ፡ ያለው ነገሩ ፡ ሊያከትም ፡ በቅርብ ፡ ነው ፡ ያለው ጌታም ፡ ከተፍ ፡ ሊል ፡ በቅርብ ፡ ነው ፡ ያለው አዝ ዘመኑ ፡ ፈጠነ ፡ ሮጠ ፡ ገሰገሰ የጌታችን ፡ መምጫ ፡ ጊዜያቱ ፡ ደረሰ ሰዎች ፡ ቶሎ ፡ በሉ ፡ መከሩን ፡ ሰብስቡ የተጣለብንን ፡ አደራ ፡ አስቡ ሰማያት ፡ ሲከብዱ ፡ ደመናው ፡ ሲጠቁር ምድራችን ፡ ስታምር ፡ ነገር ፡ ሲቀያየር ምን ፡ አዚም ፡ ኖረብን ፡ እንዳናይ ፡ ጊዜ ፡ አጥሮን ተው ፡ ነቃ ፡ እንበል ፡ እናቁም ፡ አንቅልፍን አዝ ዘመኑ ፡ ፈጠነ ፡ ሮጠ ፡ ገሰገሰ የጌታችን ፡ መምጫ ፡ ጊዜያቱ ፡ ደረሰ ሰዎች ፡ ቶሎ ፡ በሉ ፡ መከሩን ፡ ሰብስቡ የተጣለብንን ፡ አደራ ፡ አስቡ ሰዉ ፡ ሲተራመስ ፡ ሞትን ፡ ለመሳለም ከአምላክ ፡ ተለይቶ ፡ በኃጢያት ፡ ሲታመን ጠቢቡ ፡ እንኳን ፡ ሲስት ፡ በሰይጣን ፡ ሲታለል ተነሱ ፡ አንናገር ፡ ለነፍስ ፡ እንታገል አዝ ዘመኑ ፡ ፈጠነ ፡ ሮጠ ፡ ገሰገሰ የጌታችን ፡ መምጫ ፡ ጊዜያቱ ፡ ደረሰ ሰዎች ፡ ቶሎ ፡ በሉ ፡ መከሩን ፡ ሰብስቡ የተጣለብንን ፡ አደራ ፡ አስቡ ለራሱ ፡ ያልሞተ ፡ እራሱን ፡ ያልከዳ ጌታ ፡ የማይገዛው ፡ ለኃጥያት ፡ ያልታገለ በምኑ ፡ ይመስክር ፡ ልቡ ፡ ይንቀጠቀጣል ዋጋም ፡ ክፈል ፡ ሲባል ፡ ትቶ ፡ ይፈረጥጣል አዝ ዘመኑ ፡ ፈጠነ ፡ ሮጠ ፡ ገሰገሰ የጌታችን ፡ መምጫ ፡ ጊዜያቱ ፡ ደረሰ ሰዎች ፡ ቶሎ ፡ በሉ ፡ መከሩን ፡ ሰብስቡ የተጣለብንን ፡ አደራ ፡ አስቡ

