Gubae

የሰራልኝን ድንቅ

Yeseralegnen Denq

ተስፋዬ ጋቢሶ · ክርስቲያን ተሻገረ

ዘማሪ ፡ ተስፋዬ ጋቢሶ ርዕስ ፡ የሰራልኝን ፡ ድንቅ አልበም ፡ ክርስቲያን ፡ ተሻገረ አዝ የሰራልኝን ፡ ድንቅ ፡ ታሪኩን ፡ ላውጋችሁ ሰዎች ፡ እስኪ ፡ ስሙ ፡ ትምህርት ፡ ይሁናችሁ በጌታ ፡ ይታመን ፡ ይጽናና ፡ ልባችሁ (፪) በእለት ፡ እርምጃዬ ፡ እግሬን ፡ የሱስ ፡ ቀድሞ ምህረቱን ፡ አብዝቶ ፡ ተዓምራቱን ፡ ደግሞ አሳየኝ ፡ አምላኬ ፡ የከበረ ፡ ነገር እንደዚህ ፡ ሊመራኝ ፡ ወደ ፡ ፃድቃን ፡ አገር (፪x) አዝ የሰራልኝን ፡ ድንቅ ፡ ታሪኩን ፡ ላውጋችሁ ሰዎች ፡ እስኪ ፡ ስሙ ፡ ትምህርት ፡ ይሁናችሁ በጌታ ፡ ይታመን ፡ ይጽናና ፡ ልባችሁ (፪) በቀኝ ፡ በግራዬ ፡ አድፍጦ ፡ አድብቶ መልካም ፡ መሰል ፡ አጥፊ ፡ ወጥመዱን ፡ ዘርግቶ ጌታ ፡ ግን ፡ ሲያድነኝ ፡ በጦር ፡ ተደራጅቶ ዲያብሎስ ፡ ሊያጠቃኝ ነበር ፡ ተሰናድቶ (፪x) አዝ የሰራልኝን ፡ ድንቅ ፡ ታሪኩን ፡ ላውጋችሁ ሰዎች ፡ እስኪ ፡ ስሙ ፡ ትምህርት ፡ ይሁናችሁ በጌታ ፡ ይታመን ፡ ይጽናና ፡ ልባችሁ (፪) እርሱ ፡ ቅጥር ፡ ሲቀጥር ፡ በእምላኬ ፡ እየዘለልኩ ወጥመድ ፡ ሲዘረጋ ፡ እኔም ፡ እያመለጥኩ በእኔ ፡ ብርታት ፡ ሳይሆን ፡ በጌታ ፡ እየታመንኩ ሩጫ ፡ ቀጥላለሁ ፡ ሁሉን ፡ እያሸነፍኩ (፪x) አዝ የሰራልኝን ፡ ድንቅ ፡ ታሪኩን ፡ ላውጋችሁ ሰዎች ፡ እስኪ ፡ ስሙ ፡ ትምህርት ፡ ይሁናችሁ በጌታ ፡ ይታመን ፡ ይጽናና ፡ ልባችሁ (፪) በዘለዓለም ፡ መድህን ፡ ከጥልቁ ፡ ወጥቼ ከአባት ፡ ከእናት ፡ ዘመድ ፡ የሚበልጥ ፡ አግኝቼ በአህዛብ ፡ መሃከል ፡ ለርሱ ፡ ዘምራለሁ የከበረ ፡ ሥሙን ፡ አመሰግናለሁ (፪x) አዝ የሰራልኝን ፡ ድንቅ ፡ ታሪኩን ፡ ላውጋችሁ ሰዎች ፡ እስኪ ፡ ስሙ ፡ ትምህርት ፡ ይሁናችሁ በጌታ ፡ ይታመን ፡ ይጽናና ልባችሁ (፪×)

ተስፋዬ ጋቢሶ · ሁሉም ዘማሪዎች