የሚቋቋምህ ማንም የለም
Yemiquaquameh Manem Yelem
ተስፋዬ ጋቢሶ · የናዝሬቱ ኢየሱስ
አዝ፦ የሚቋቋምህ ፡ ማንም ፡ የለም ፈቃድህ ፡ በእኛ ፡ ይሙላ ፡ ይፈፀም ታላቅነትህም ፡ ይነገር ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ክበር (፪x) ሕዝብህን ፡ ከምድር ፡ ዋጅተሃል ታላቅ ፡ ሥራ ፡ ጀምረሃል ሀሳብህ ፡ አይከለከልም ፅድቅህ ፡ እውነትህ ፡ ይለምልም አዝ፦ የሚቋቋምህ ፡ ማንም ፡ የለም ፈቃድህ ፡ በእኛ ፡ ይሙላ ፡ ይፈፀም ታላቅነትህም ፡ ይነገር ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ክበር በየደረስንበት ፡ ስፍራ ስራችንን ፡ አንተ ፡ ሥራ እጃችን ፡ ሳይዝል ፡ ስይደክም ዛሬም ፡ እንደ ፡ ወትሮ ፡ ቅደም አዝ፦ የሚቋቋምህ ፡ ማንም ፡ የለም ፈቃድህ ፡ በእኛ ፡ ይሙላ ፡ ይፈፀም ታላቅነትህም ፡ ይነገር ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ክበር ስለተነቀፈው ፡ ሥምህ በምርኮ ፡ ስላለው ፡ ሕዝብህ ይዘርጋ ፡ ያ ፡ ፅኑ ፡ ክንድህ ዛሬም ፡ ይንሰራፋ ፡ ክብርህ አዝ፦ የሚቋቋምህ ፡ ማንም ፡ የለም ፈቃድህ ፡ በእኛ ፡ ይሙላ ፡ ይፈፀም ታላቅነትህም ፡ ይነገር ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ክበር ወድቀን ፡ በፊትህ ፡ ስንጮህ ክንድህ ፡ ከፍ ፡ ይበል ፡ ጌታ ፡ ሆይ ሰማይ ፡ ምድሩ ፡ ያከብርሃል ሁሉም ፡ በፊትህ ፡ ይሰግዳል አዝ፦ የሚቋቋምህ ፡ ማንም ፡ የለም ፈቃድህ ፡ በእኛ ፡ ይሙላ ፡ ይፈፀም ታላቅነትህም ፡ ይነገር ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ክበር (፪x)

