Gubae

የኃያላን ሁሉ ኃያል

Yehayalan Hulu Hayal

ተስፋዬ ጋቢሶ · አዎን ይሆናል

ሰማይን ፡ የሰራ ፡ የምድርም ፡ ፈጣሪ በዘለዓለም ፡ ዙፋን ፡ ለዘለዓለም ፡ ኗሪ ገናናነትህን ፡ ሰማያት ፡ ያውቃሉ ምድርና ፡ ሞላዋም ፡ ይመሰክራሉ። የኃያላን ፡ ሁሉ ፡ ኃያል ፡ ነህ የነገሥታት ፡ ሁሉ ፡ ንጉሥ ፡ ነህ የጌቶችም ፡ ሁሉ ፡ ጌታ ፡ ነህ ባለ ፡ ታላቅ ፡ ግርማ ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነህ። በነገስህ ፡ ጊዜ ፡ ክብርህን ፡ ስትለብስ ለተጠቃው ፡ ህዝብህ ፡ ፊትህን ፡ ስትመልስ ድንቅ ፡ አድራጐትህን ፡ በምድር ፡ ስታደርግ በጽድቅህ ፡ ስትፈርድ ፡ አመጻን ፡ ስትጠርግ። የኃያላን ፡ ሁሉ ፡ ኃያል ፡ ነህ የነገሥታት ፡ ሁሉ ፡ ንጉሥ ፡ ነህ የጌቶችም ፡ ሁሉ ፡ ጌታ ፡ ነህ ባለ ፡ ታላቅ ፡ ግርማ ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነህ። ቃልህን ፡ ስትሰጥ ፡ በሲና ፡ ተራራ በልጆችህ ፡ ሰፈር ፡ በበረሃው ፡ ስፍራ በክብር ፡ እሳትህ ፡ ተራራውን ፡ አጤስከው በመረጥካቸው ፡ ፊት ፡ ክብርህን ፡ ገለጽከው የኃያላን ፡ ሁሉ ፡ ኃያል ፡ ነህ የነገሥታት ፡ ሁሉ ፡ ንጉሥ ፡ ነህ የጌቶችም ፡ ሁሉ ፡ ጌታ ፡ ነህ ባለ ፡ ታላቅ ፡ ግርማ ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነህ። የተዳፈሩህን ፡ የተነሱብህን ልክህን ፡ ሳያውቁ ፡ የታጠቁብህን እየቀጣሃቸው ፡ ተረቶች ፡ ሆነዋል ተፈርተህ ፡ ተከብረህ ፡ አንተ ፡ ግን ፡ ኖረሃል። የኃያላን ፡ ሁሉ ፡ ኃያል ፡ ነህ የነገሥታት ፡ ሁሉ ፡ ንጉሥ ፡ ነህ የጌቶችም ፡ ሁሉ ፡ ጌታ ፡ ነህ ባለ ፡ ታላቅ ፡ ግርማ ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነህ። x2

ተስፋዬ ጋቢሶ · ሁሉም ዘማሪዎች