ተነሥ
Tenes
ተስፋዬ ጋቢሶ · የናዝሬቱ ኢየሱስ
ዘማሪ=ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ ርዕስ ተነሥ አልበም የናዝሬቱ ኢየሱስ አዝ ተነሥ (፬x) የእግዚአብሔር ክንድ እንደ ጥንቱ ተነሥ ኃይልንም ልበስ እንደ ጥንቱ ተነሥ (፪x) ሕዝብህ በምድረ ግብፅ ኑሮ ቢመራቸው ከበግ ጥበቃ ላይ ሙሴን የጠራኸው የዘመናት ንጉሥ እግዚአብሔር ሆይ ዘንዶውን የወጋህ አንተ አይደለህም ወይ አዝ ተነሥ (፬x) የእግዚአብሔር ክንድ እንደ ጥንቱ ተነሥ ኃይልንም ልበስ እንደ ጥንቱ ተነሥ የሳተም ይመለስ የዛለም ይበርታ የኃጢአት ምርኮኛ ከእስራት ይፈታ ክንድህን ስንጠብቅ በናፍቆት ዝለናል እስኪ አንድ ጊዜ ጐብኘን ተጠምተናል አዝ ተነሥ (፬x) የእግዚአብሔር ክንድ እንደ ጥንቱ ተነሥ ኃይልንም ልበስ እንደ ጥንቱ ተነሥ ያለፉት ባሮችህ አስከብረውሃል ኃይልህ ከላይ ሲወርድ ከአንበሳ ገጥመዋል አንካሶች ሮጠዋል ጋኔሎች ወጥተዋል ጊዜ እይለውጥህም እኛም አይተንሃል አዝ ተነሥ (፬x) የእግዚአብሔር ክንድ እንደ ጥንቱ ተነሥ ኃይልንም ልበስ እንደ ጥንቱ ተነሥ

