ሥራህ ያመሰግንሃል
Serah Yamesegenehal
ተስፋዬ ጋቢሶ · አዎን ይሆናል
ዘማሪ ፡ ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ ርዕስ ፡ ሥራህ ፡ ያመሰግንሃል ሥራህ ፡ ያመሰግንሃል ቅዱሳን ፡ ያከብሩሃል ጌትነትህም ፡ ገብቷቸው ተንበርክኳል ፡ ጉልበታቸው አዝ ሃሌሉያ ፡ ተመስገን ጌታ ፡ ተመስገን ተመስገን (፫x) ኢየሱስ ፡ ተመስገን እውነትህን ፡ ጠብቀሃል ለተበደሉት ፡ ፈርደሃል የተጠቃውን ፡ ታድገሃል በማዳንህ ፡ ከፍ ፡ ብለሃል አዝ ሃሌሉያ ፡ ተመስገን ጌታ ፡ ተመስገን ተመስገን (፫x) ኢየሱስ ፡ ተመስገን ደሃ ፡ አደጉን ፡ ተቀብለህ ለተራበ ፡ ምግብን ፡ ሰጥተህ ምጻተኛ ፡ አስጠግተሃል ግዞተኛውን ፡ ፈተሃል አዝ ሃሌሉያ ፡ ተመስገን ጌታ ፡ ተመስገን ተመስገን (፫x) ኢየሱስ ፡ ተመስገን የተቀደሰ ፡ ሥምህን በዜማ ፡ ቅኔ ፡ ላመስግን በአንተ ፡ ሆኖልኝ ፡ የመዳን ፡ ቀን ስለወጣሁ ፡ ከሰቀቀን አዝ ሃሌሉያ ፡ ተመስገን ጌታ ፡ ተመስገን ተመስገን (፫x) ኢየሱስ ፡ ተመስገን

