Gubae

ስለወደድከኝ እወድሃለሁ

Selewededkegn Wedehalew

ተስፋዬ ጋቢሶ · የናዝሬቱ ኢየሱስ

ለምን ፡ ወደድከኝ ፡ አልልህም ፡ በእርግጥ ፡ ወደኸኛል የፍቅርህ ፡ መግለጫ ፡ ይሄ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ተወግተሃል አንተ ፡ ለእኔ ፡ የሆንከውን ፡ ያህል ፡ እኔ ፡ ለአንተ ፡ አልሆንኩም ምን ፡ ያህል ፡ እንደሆነ ፡ አላውቅም ፡ ለክቼ ፡ አላየሁም ግን ፡ አንድ ፡ ነገር ፡ አውቃለሁ ስለወደድከኝ ፡ ወድሃለሁ (፪x) አዝ ከእርግማን ፡ ስለ ፡ ዋጀኸኝ ፡ ሞተህ ፡ ሸክሜን ፡ ስለ ፡ ወሰድክ በመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ስለ ፡ ሞላኸኝ ፡ ነፍሴን ፡ ስለ ፡ ባረክ ፀጋህን ፡ አብዝተህ ፡ ስለ ፡ ሰጠኸኝ ፡ ከቶም ፡ ስላልተውከኝ ምን ፡ ያህል ፡ እንደሆነ ፡ አላውቅም ፡ ለክቼም ፡ አላየሁም ግን ፡ አንድ ፡ ነገር ፡ አውቃለሁ ስለወደድከኝ ፡ ወድሃለሁ (፪x) አዝ ደስ ፡ ላሰኝህ ፡ እቀናለሁ ፡ በሕይወቴ ፡ ላከብርህ ሆኖም ፡ ከቶ ፡ አልጠቀምኩህም ፡ ሁሌ ፡ ሳሳዝንህ ይልቅ ፡ ብዙ ፡ አድክሜሃለሁ ፡ የትም ፡ እየቀረሁ ብዙም ፡ ስላላፈራሁ ፡ ኢየሱስ ፡ ከፍቶኝ ፡ አለቅሳለሁ አዝ ምን ፡ ያህል ፡ እንደሆነ ፡ አላውቅም ፡ ለክቼም ፡ አላየሁም ግን ፡ አንድ ፡ ነገር ፡ አውቃለሁ ስለወደድከኝ ፡ ወድሃለሁ (፪x)

ተስፋዬ ጋቢሶ · ሁሉም ዘማሪዎች