ነፍሴ ሆይ
Nefsie Hoy
ተስፋዬ ጋቢሶ · የናዝሬቱ ኢየሱስ
ከጥፋት ፡ ጉድጓድ ፡ ውስጥ ፡ ከረግርግ ፡ ጭቃ ፡ ያወጣኝ እግሬን ፡ በድንጋይ ፡ ላይ ፡ አቁሞ ፡ ያፀናኝ በፀጋው ፡ ደግፎ ፡ በሕይወት ፡ ያኖረኝ ከክፉ ፡ ፍላጻ ፡ በእጁ ፡ የከለለኝ አዝ ነፍሴ ፡ ሆይ ፡ እግዚአብሔር ፡ አምላክ ፡ ነውና ፡ ስገጂለት መሀሪው ፡ ጌታዬ ፡ ምሥጋና ፡ ይብዛለት በሕይወቴ ፡ ሁሉ ፡ እኔም ፡ ልገዛለት ቸርነቱን ፡ ልንገር ፡ ምህረቱን ፡ ልዘምር ቅኔን ፡ ልቀኝለት ፡ ኦ ፡ ቅኔን ፡ ልቀኝለት ድካምን ፡ ህመምን ፡ ቁስልን ፡ ስብራትን ፡ አይቶ ዘመድ ፡ ርቆ ፡ ሲቆም ፡ ኢየሱስ ፡ ተጠግቶ በፍቅር ፡ አክሞ ፡ ሕይወትን ፡ ያድሳል ለውለታው ፡ ምላሽ ፡ ከቶ ፡ ምን ፡ ይገኛል አዝ ነፍሴ ፡ ሆይ ፡ እግዚአብሔር ፡ አምላክ ፡ ነውና ፡ ስገጂለት መሀሪው ፡ ጌታዬ ፡ ምሥጋና ፡ ይብዛለት በሕይወቴ ፡ ሁሉ ፡ እኔም ፡ ልገዛለት ቸርነቱን ፡ ልንገር ፡ ምህረቱን ፡ ልዘምር ቅኔን ፡ ልቀኝለት ፡ ኦ ፡ ቅኔን ፡ ልቀኝለት የጫንቃዬን ፡ ሸክም ፡ ጌታዬ ፡ ደርሶ ፡ ጣለልኝ የዕዳዬን ፡ ጽሕፈት ፡ በሞቱ ፡ ሻረልኝ ምህረቱ ፡ ድንቅ ፡ ነው ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ያሳየው ከእግሩ ፡ ሥር ፡ ወድቄ ፡ ጌታዬን ፡ ላክብረው አዝ ነፍሴ ፡ ሆይ ፡ እግዚአብሔር ፡ አምላክ ፡ ነውና ፡ ስገጂለት መሀሪው ፡ ጌታዬ ፡ ምሥጋና ፡ ይብዛለት በሕይወቴ ፡ ሁሉ ፡ እኔም ፡ ልገዛለት ቸርነቱን ፡ ልንገር ፡ ምህረቱን ፡ ልዘምር ቅኔን ፡ ልቀኝለት ፡ ኦ ፡ ቅኔን ፡ ልቀኝለት

