Gubae

ላመስግንህ ዛሬም

Lamesgeneh Zariem

ተስፋዬ ጋቢሶ · እግዚአብሔር መንፈስ ነው

ዘማሪ ፡ ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ ርዕስ ፡ ላመስግንህ ፡ ዛሬም አልበም ፡ እግዚአብሔር ፡ መንፈስ ፡ ነው ትንፋሼንና ፡ መንገዴ ፡ ሁሉ ፡ በእጅህ ፡ ይዘህ እንደ ፡ ዓይንህ ፡ ብሌን ፡ አርገህ ፡ ለእኔ ፡ ተጠንቅቀህ ከሚጐዳኝ ፡ ነገር ፡ ዘወትር ፡ ጋረድክ ፡ ሰውረህ ተመሥገን ፡ ከማለት ፡ ሌላ ፡ ለአንተ ፡ ምን ፡ ልክፈልህ አዝ ላመስግንህ ፡ ዛሬም ፡ የእኔ ፡ ጌታ ስለማይነገር ፡ ስጦታህ ፡ ስላማይቆጠር ፡ ውለታህ በእውነት ፡ አንተ ፡ ታማኝ ፡ ነህ ዘላለም ፡ ይወደስ ፡ ይክበር ፡ ታላቅ ፡ ሥምህ በሀዘን ፡ ስመታ ፡ ሲከፋኝም ፡ አንዳንድ ፡ ጊዜ ከብዶ ፡ ሲጫጫነኝ ፡ ሲደራረብብኝ ፡ ትካዜ የመፅናናት ፡ ጌታ ፡ ማን ፡ እንደ ፡ አንተ ፡ ደረሰልኝ የልቤን ፡ ተካፍሎ ፡ አይዞህ ፡ ሊለኝ ፡ ሊያበረታኝ አዝ ላመስግንህ ፡ ዛሬም ፡ የእኔ ፡ ጌታ ስለማይነገር ፡ ስጦታህ ፡ ስላማይቆጠር ፡ ውለታህ በእውነት ፡ አንተ ፡ ታማኝ ፡ ነህ ዘላለም ፡ ይወደስ ፡ ይክበር ፡ ታላቅ ፡ ሥምህ ራሴን ፡ አውቀው ፡ አለሁ ፡ እጅግ ፡ አስቀያሚ ፡ ነበርኩ ምስኪን ፡ አላማ ፡ ቢስ ፡ በኃጥያት ፡ የተቅበዘበዝኩ ግን ፡ እንዲያው ፡ ወደኸኝ ፡ ሰው ፡ ሆኛለሁ ፡ በአንተ ፡ ብርታት በቂ ፡ ቃል ፡ የለኝም ፡ ልገልፅ ፡ የውለታህን ፡ ብዛት አዝ ላመስግንህ ፡ ዛሬም ፡ የእኔ ፡ ጌታ ስለማይነገር ፡ ስጦታህ ፡ ስላማይቆጠር ፡ ውለታህ በእውነት ፡ አንተ ፡ ታማኝ ፡ ነህ ዘላለም ፡ ይወደስ ፡ ይክበር ፡ ታላቅ ፡ ሥምህ አህዛብ ፡ ባያውቁህም ፡ የእኔ ፡ ነፍስ ፡ ግን ፡ ታውቅሃለች የፍቅር ፡ ፊትህን ፡ በእየለት ፡ ትናፍቃለች ያለ ፡ አባትነትህ ፡ መኖር ፡ ከቶ ፡ አይሆንላትም መሳይ ፡ አጭበርባሪ ፡ ሁሉ ፡ ከአንተ ፡ አይነጥላትም አዝ ላመስግንህ ፡ ዛሬም ፡ የእኔ ፡ ጌታ ስለማይነገር ፡ ስጦታህ ፡ ስላማይቆጠር ፡ ውለታህ በእውነት ፡ አንተ ፡ ታማኝ ፡ ነህ ዘላለም ፡ ይወደስ ፡ ይክበር ፡ ታላቅ ፡ ሥምህ

ተስፋዬ ጋቢሶ · ሁሉም ዘማሪዎች