Gubae

እግዚአብሔር ሲረዳ

Egziabhier Sireda

ተስፋዬ ጋቢሶ · የናዝሬቱ ኢየሱስ

በሕይወት ፡ ጐዳና ፡ ፈተና ፡ ቢበዛም  ጌታን ፡ እየጠራ ፡ ንጹህ ፡ ሰው ፡ አይጠፋም  እጄን ፡ ያዘኝ ፡ ብሎ ፡ ሲጮህ ይሰማዋል  ከረግረግ ፡ አውጥቶ ፡ በድል ፡ ይመራዋል አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ሲረዳ ፡ ከሰማያት ፡ ወርዶ በደልን ፡ ሲያስወግድ ፡ በቅንነት ፡ ፈርዶ አላያችሁም ፡ ወይ ፡ ወጥመዱ ፡ ሲሰበር ምርኮኛው ፡ ተለቆ ፡ ማዳኑን ፡ ሲናገር ችግረኛውን ፡ ሊውጥ ፡ ጠላት ፡ ሲገዳደር በሚያስፈራራ ፡ ቃል ፡ በትዕቢት ፡ ሲናገር ደርሶ ፡ የሚታደግ ፡ እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ ነው በሰው ፡ መታመን ፡ ግን ፡ የከንቱ ፡ ከንቱ ፡ ነው አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ሲረዳ ፡ ከሰማያት ፡ ወርዶ በደልን ፡ ሲያስወግድ ፡ በቅንነት ፡ ፈርዶ አላያችሁም ፡ ወይ ፡ ወጥመዱ ፡ ሲሰበር ምርኮኛው ፡ ተለቆ ፡ ማዳኑን ፡ ሲናገር ያለውን ፡ ተነጥቆ ፡ ሁሉን ፡ ነገር ፡ አጥቶ ከአጠገቡ ፡ የሚቆም ፡ ጌታ ፡ ብቻ ቀርቶ በእንግድነት ፡ አገር ፡ ተገፍቶ ፡ ለሚያልፈው ተስፋው ፡ መሰረቱ ፡ አምላኩ ፡ ብቻ ፡ ነው አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ሲረዳ ፡ ከሰማያት ፡ ወርዶ በደልን ፡ ሲያስወግድ ፡ በቅንነት ፡ ፈርዶ አላያችሁም ፡ ወይ ፡ ወጥመዱ ፡ ሲሰበር ምርኮኛው ፡ ተለቆ ፡ ማዳኑን ፡ ሲናገር የቅዱሳን ፡ ረድኤት ፡ ከሰማይ ፡ ይመጣል ዘመናትን ፡ ቆጥሮ ፡ ጌታ ፡ ይመለሳል የልጆቹን ፡ እንባ ፡ ከዓይናቸው ፡ ያብሳል ክብርና ፡ ምሥጋና ፡ ለሥሙ ፡ ይሆናል አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ሲረዳ ፡ ከሰማያት ፡ ወርዶ በደልን ፡ ሲያስወግድ ፡ በቅንነት ፡ ፈርዶ አላያችሁም ፡ ወይ ፡ ወጥመዱ ፡ ሲሰበር ምርኮኛው ፡ ተለቆ ፡ ማዳኑን ፡ ሲናገር

ተስፋዬ ጋቢሶ · ሁሉም ዘማሪዎች