በእውነት አሳደገን
Bewnet Asadegen
ተስፋዬ ጋቢሶ · የናዝሬቱ ኢየሱስ
ዘማሪ ፡ ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ ርዕስ ፡ በእውነት ፡ አሳድገ አልበም ፡ የናዝሬቱ ፡ ኢየሱስ አዝ በእውነት ፡ አሳድገን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ በፍቅር በከንቱ ፡ መታበያችን ፡ ይቅር በእውነት ፡ አሳድገን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ በፍቅር በክርስትናችን ፡ ዕድሜ ፡ ቆጥረን በልምምዳችን ፡ ኮርተን በትህትና ፡ መማሩ ፡ ቀረና እድገታችን ፡ ቆመ ፡ ታበይንና አዝ በእውነት ፡ አሳድገን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ በፍቅር በከንቱ ፡ መታበያችን ፡ ይቅር በእውነት ፡ አሳድገን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ በፍቅር ባስተያየታችን ፡ ጠቢባን ፡ ነን ትንኝን ፡ እናጠራለን ራሳችንን ፡ ማንጻት ፡ ሳይቻለን የሌላውን ፡ ጉድፍ ፡ እናያለን አዝ በእውነት ፡ አሳድገን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ በፍቅር በከንቱ ፡ መታበያችን ፡ ይቅር በእውነት ፡ አሳድገን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ በፍቅር ማደጋችንን ፡ እዩልን ፡ እያልን በከንቱም ፡ እየታበይን አንተንም ፡ በዚህ ፡ እያሳዘንን ሳይታወቀን ፡ ስንቶችን ፡ ጐዳን አዝ በእውነት ፡ አሳድገን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ በፍቅር በከንቱ ፡ መታበያችን ፡ ይቅር በእውነት ፡ አሳድገን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ በፍቅር እንደ ፡ ሕጻናት ፡ የዋሆች ፡ አርገን ንጹህ ፡ ልብን ፡ መልስልን ዓይናችንን ፡ እየገለጥህ አንተው ፡ አመላልሰን ፡ በብርሃንህ አዝ በእውነት ፡ አሳድገን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ በፍቅር በከንቱ ፡ መታበያችን ፡ ይቅር በእውነት ፡ አሳድገን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ በፍቅር በቃል ፡ በስርአት ፡ ሙታን ፡ ሆነን በፍቅር ፡ እየታነፅን በእውነት ፡ እንደግ ፡ ወደ ፡ ኢየሱስ እየታበይን ፡ እንደምን ፡ እንነስ አዝ በእውነት ፡ አሳድገን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ በፍቅር በከንቱ ፡ መታበያችን ፡ ይቅር በእውነት ፡ አሳድገን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ በፍቅር

