አቤቱ መባረኬን ባርከኝ
Abietu Mebareken Barken
ተስፋዬ ጋቢሶ · አቤቱ መባረኬን ባርከኝ
ዘማሪ ፡ ተስፋዬ ጋቢሶ ርዕስ ፡ አቤቱ ፡ መባረክን ፡ ባርከን አልበም ፡ አቤቱ ፡ መባረክን ፡ ባርከን አዝ አቤቱ ፡ መባረክን ፡ ባርከን አገራችንን ፡ አስፋ እጅህም ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ትሁን አንተ ፡ ነህ ፡ የእኛ ፡ ተስፋ ያቤጽንም ፡ ሰምተሃል ፡ እንደዚህ ፡ ሲለምንህ ነፍሱን ፡ ባርከህለታል ፡ አገሩንም ፡ አስፍተህ አዝ አቤቱ ፡ መባረክን ፡ ባርከን አገራችንን ፡ አስፋ እጅህም ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ትሁን አንተ ፡ ነህ ፡ የእኛ ፡ ተስፋ በልጅህ ፡ ስቃይና ፡ በጣር ፡ የተወለድን እኛም ፡ ፍሬዎችህ ፡ ነን ፡ አስባስበህ ፡ ጠብቀን አዝ አቤቱ ፡ መባረክን ፡ ባርከን አገራችንን ፡ አስፋ እጅህም ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ትሁን አንተ ፡ ነህየእኛ ፡ ተስፋ ከፊትህ ፡ አትጣለን ፡ እንማጸንሃለን በሞገስህ ፡ አስበን ፡ በምህረትህ ፡ ጐብኘን አዝ አቤቱ ፡ መባረክን ፡ ባርከን አገራችንን ፡ አስፋ እጅህም ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ትሁን አንተ ፡ ነህ ፡ የእኛ ፡ ተስፋ ሰማያቱም ፡ ይከፈቱ ፡ መንፈስህ ፡ ይፍሰስልን ሕይወታችን ፡ ትረስርስ ፡ ነፍሳችን ፡ ትጥገብልን አዝ አቤቱ ፡ መባረክን ፡ ባርከን አገራችንን ፡ አስፋ እጅህም ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ትሁን አንተ ፡ ነህ ፡ የእኛ ፡ ተስፋ ብቻችንን ፡ አንቅር ፡ አብዛን ፡ እየባረክህ አበልጽገን ፡ በፀጋህ ፡ ታደገን ፡ በቃልህ አዝ አቤቱ ፡ መባረክን ፡ ባርከን አገራችንን ፡ አስፋ እጅህም ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ትሁን አንተ ፡ ነህ ፡ የእኛ ፡ ተስፋ እግዚአብሔርን ፡ በማወቅ ፡ ምድር ፡ እስክትሞላ ምልጃችን ፡ ይቀጥላል ፡ ጉልበታችን ፡ ሳይላላ አዝ አቤቱ ፡ መባረክን ፡ ባርከን አገራችንን ፡ አስፋ እጅህም ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ትሁን አንተ ፡ ነህ ፡ የእኛ ፡ ተስፋ

