Gubae

Yehayalan Hayal Yegna Gieta

ተስፋዬ ቻላ · ባማረ ቅኔ

ዘማሪ ፡ ተስፋዬ ፡ ጫላ ርዕስ ፡ የኃያላን ፡ ኃያል ፡ የእኛ ፡ ጌታ አልበም ፡ ባማረ ፡ ቅኔ አዝ የኃያላን ፡ ኃያል ፡ የእኛ ፡ ጌታ በሰልፍ ፡ በወጀቡ ፡ የበረታ እንደ ፡ እርሱ ፡ የሚሆን ፡ ማንም ፡ የለም ይክበር ፡ ይንገሥ ፡ ለዘላለም (፪x) ብዙ ፡ ሃያላኖች ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ ነበሩ እንድ ፡ ዘመን ፡ ታይተው ፡ ጠፍተው ፡ በዚያው ፡ ቀሩ የእኛ ፡ ኢየሱስ ፡ ግን ፡ መቃብር ፡ ፈንቅሎ ከበረ ፡ በሰማይ ፡ አሜን ፡ በሞት ፡ ላይ ፡ አይሎ አዝ የኃያላን ፡ ኃያል ፡ የእኛ ፡ ጌታ በሰልፍ ፡ በወጀቡ ፡ የበረታ እንደ ፡ እርሱ ፡ የሚሆን ፡ ማንም ፡ የለም ይክበር ፡ ይንገሥ ፡ ለዘላለም የኃያላን ፡ ኃያል ፡ የነገሥታት ፡ ንጉሥ ማነው ፡ የሚመስለው ፡ የናዝሬቱን ፡ ኢየሱስ ማህተቡን ፡ ሊፈታ ፡ የቻለው ፡ እርሱ ፡ ነው ይክበር ፡ ዛሬም ፡ አሜን ፡ አዎ ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው አዝ የኃያላን ፡ ኃያል ፡ የእኛ ፡ ጌታ በሰልፍ ፡ በወጀቡ ፡ የበረታ እንደ ፡ እርሱ ፡ የሚሆን ፡ ማንም ፡ የለም ይክበር ፡ ይንገሥ ፡ ለዘላለም (፪x) ማንም ፡ ያልቻለውን ፡ መጋረጃ ፡ ቀዶ ወንጌልን ፡ ሰበከ ፡ ወደ ፡ ሲኦል ፡ ወርዶ ለታሰሩት ፡ ሰላም ፡ መፈታት ፡ አወጀ በመስቀል ፡ ላይ ፡ ሞቶ ፡ በደሙ ፡ እኛን ፡ ዋጀ አዝ የኃያላን ፡ ኃያል ፡ የእኛ ፡ ጌታ በሰልፍ ፡ በወጀቡ ፡ የበረታ እንደ ፡ እርሱ ፡ የሚሆን ፡ ማንም ፡ የለም ይክበር ፡ ይንገሥ ፡ ለዘላለም የኃያላን ፡ ኃያል ፡ የእኛ ፡ ጌታ በሰልፍ ፡ በወጀቡ ፡ ኃያል ፡ ንጉሥ እንደ ፡ አንተ ፡ የሚሆን ፡ ማንም ፡ የለም ክበር ፡ ንገሥ ፡ ለዘላለም አጋንንት ፡ በሥሙ ፡ ይታዘዙለታል ሰማይ ፡ ምድር ፡ ሁሉ ፡ ለክብሩ ፡ ዝቅ ፡ ይላል ማዕበል ፡ ወጀቡን ፡ ባሕሩን ፡ ይከፍላል ጌት ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ አዎ ፡ ዘለዓለም ፡ ይገዛል አዝ የኃያላን ፡ ኃያል ፡ የእኛ ፡ ጌታ በሰልፍ ፡ በወጀቡ ፡ የበረታ እንደ ፡ እርሱ ፡ የሚሆን ፡ ማንም ፡ የለም ይክበር ፡ ይንገሥ ፡ ለዘላለም (፪x) እንደ ፡ እርሱ ፡ የሆነ ፡ ማንም ፡ የለም ይክበር ፡ ይንገሥ ፡ ለዘላለም እንደ ፡ አንተ ፡ የሚሆን ፡ ማንም ፡ የለም ይክበር ፡ ይንገሥ ፡ ለዘላለም (፪x)

ተስፋዬ ቻላ · ሁሉም ዘማሪዎች