Tamagneneteh Bezu Mehereteh Lenie
ተስፋዬ ቻላ · ልባርከው ጌታዬን ልባርከው
ዘማሪ ፡ ተስፋዬ ፡ ጫላ ርዕስ ፡ ታማኝነትህ ፡ ብዙ አልበም ፡ ልባርከው ፡ ጌታዬን ታማኝነትህ ፡ ብዙ ፡ ምህረትህ ፡ ለልጅ ፡ ልጅ ፡ ነው አንተን ፡ ተስፋ ፡ አድርጐ ፡ ያፈረ ፡ ሰው ፡ ማን ፡ ነው ሁሉንም ፡ በስዓቱ ፡ ውብ ፡ አድርገህ ፡ ትሰራለህ አማካሪ ፡ አትፈልግም ፡ ብቻህን ፡ ኤልሻዳይ (ኢየሱስ) ነህ (፪×) በመከራ ፡ ቀን ፡ ስምህን ፡ ጠርቶ ፡ ማን ፡ ከቶ ፡ አፍሮ ፡ ያውቃል ዓይንህ ፡ ግሩም ፡ ነው ፡ በሰማይ ፡ ምስኪኑን ፡ ይመለከታል ታማኝነትህ ፡ የበዛ ፡ ምህረትህ ፡ ወደር ፡ የሌለው አንተን ፡ ተስፋ ፡ ላደረጉ ፡ እርግማኑ ፡ በረከት ፡ ነው አዝ ታማኝነትህ ፡ ብዙ ፡ ምህረትህ ፡ ለልጅ ፡ ልጅ ፡ ነው አንተን ፡ ተስፋ ፡ አድርጐ ፡ ያፈረ ፡ ሰው ፡ ማን ፡ ነው ሁሉንም ፡ በስዓቱ ፡ ውብ ፡ አድርገህ ፡ ትሰራለህ አማካሪ ፡ አትፈልግም ፡ ብቻህን ፡ ኤልሻዳይ (ኢየሱስ) ነህ (፪×) ታላቅ ፡ ተራራ ፡ በስምህ ፡ ደልዳላ ፡ ሜዳ ፡ ይሆናል ማዕበል ፡ ቃልህን ፡ ሰምቶ ፡ ፈጥኖ ፡ ያተዘዝልሃል ህዝብህን ፡ በምድረበዳ ፡ መናን ፡ መመገብ ፡ ታውቃለህ ቃልህን ፡ ለሚጠብቁ ፡ መች ፡ አንተ ፡ ታሳፍራለህ አዝ ታማኝነትህ ፡ ብዙ ፡ ምህረትህ ፡ ለልጅ ፡ ልጅ ፡ ነው አንተን ፡ ተስፋ ፡ አድርጐ ፡ ያፈረ ፡ ሰው ፡ ማን ፡ ነው ሁሉንም ፡ በስዓቱ ፡ ውብ ፡ አድርገህ ፡ ትሰራለህ አማካሪ ፡ አትፈልግም ፡ ብቻህን ፡ ኤልሻዳይ (ኢየሱስ) ነህ (፪×) ደካማው ፡ ጉልበቱ ፡ በአንተ ፡ ኃይሉ ፡ እንደንስር ፡ ታደሰ ሃያሉ ፡ ሞገስህን ፡ ሲያይ ፡ ወኔው ፡ ሃሞቱ ፡ ፈሰሰ ብላቴናው ፡ ግን ፡ በሥምህ ፡ ወንጭፍ ፡ ጠጠሩን ፡ ሰንዝሮ አየሁ ፡ ጠላቱ ፡ በቅጽበት ፡ በአደባባይ ተዘርሮ አዝ ታማኝነትህ ፡ ብዙ ፡ ምህረትህ ፡ ለልጅ ፡ ልጅ ፡ ነው አንተን ፡ ተስፋ ፡ አድርጐ ፡ ያፈረ ፡ ሰው ፡ ማን ፡ ነው ሁሉንም ፡ በስዓቱ ፡ ውብ ፡ አድርገህ ፡ ትሰራለህ አማካሪ ፡ አትፈልግም ፡ ብቻህን ፡ ኤልሻዳይ (ኢየሱስ) ነህ (፪×) ሰማይን ፡ ምድርን ፡ ስትራ ፡ ማን ፡ ቀርቦ ፡ አንተን ፡ አማክሯል ኤልሻዳይ ፡ ጌታ ፡ መሆንህን ፡ ፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ ይመሰክራል ብቻህን ፡ ለዘለዓለም ፡ ጸንተህ ፡ በዙፋንህ ፡ ላይ ፡ ነህ አንተን ፡ ታምኜ ፡ እስከዛሬ ፡ ማድጋዬ ፡ መች ፡ ጐደለ አዝ ታማኝነትህ ፡ ብዙ ፡ ምህረትህ ፡ ለልጅ ፡ ልጅ ፡ ነው አንተን ፡ ተስፋ ፡ አድርጐ ፡ ያፈረ ፡ ሰው ፡ ማን ፡ ነው ሁሉንም ፡ በስዓቱ ፡ ውብ ፡ አድርገህ ፡ ትሰራለህ አማካሪ ፡ አትፈልግም ፡ ብቻህን ፡ ኤልሻዳይ (ኢየሱስ) ነህ (፪×)

