Semeh Endemifes Zeyt New
ተስፋዬ ቻላ · ባማረ ቅኔ
ስምህ ፡ እንደሚፈስ ፡ ዘይት ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ሆይ መልካም ፡ መዓዛ ፡ አለው ፡ ውዴ ፡ ሆይ መልካም ፡ መዓዛ ፡ አለው ፡ ጌታ ፡ ሆይ ስምህን ፡ ጠርተን ፡ ተፈውሰናል ካለብን ፡ ደዌ ፡ ነጻ ፡ ወጥተናል ጅማታችንን ፡ ስምህ ፡ አራሰው ልባችን ፡ ሞልቷል ፡ ሃሌሉያ ፡ ነው ስለዚህ ፡ ጌታ ፡ ተመስገንልን አፍቅረንሃል ፡ ከውስጥ ፡ ከልብ ጎልማሳነታችንም ፡ ታድሷል በስምህ ፡ ብርታት ፡ ነጻ ፡ ወጥተናል አይምሮ ፡ አርሶ ፡ ከልብም ፡ አልፎ ያለ ፡ ሁኔታ ፡ ተድላን ፡ አልብሶ የሚጣፍጠው ፡ ሥምህ ፡ ቁልፍ ፡ ነው ደናግል ፡ ለአንተ ፡ በፍቅር ፡ ናቸው ሌሊት ፡ በምሽት ፡ ከእንቅልፍ ፡ ተነስተን ስንበረከክ ፡ አንተን ፡ ፈልገን ስምህን ፡ ጠርተን ፡ እፎይ ፡ እረካን ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ማን ፡ ይመስልሃል ማድጋችንን ፡ ዘይትህ ፡ ሞላው ያንን ፡ ስምህን ፡ ታምነን ፡ ስንጠራው ባዶ ፡ ነበር ፡ ማስሮ ፡ ዕቃችን ግን ፡ አሁን ፡ በአንተ ፡ አገኘን ለጎረቤትም ፡ ተርፏል ፡ ሰላምህ ከእኛም ፡ አልፎ ፡ ከደናግልህ ኦ ፡ ምንልህ ፡ የምንሰጥህ የለንምና ፡ ከፍ ፡ ይበል ፡ ስምህ

