Gubae

Salwedeh Yewededkegn

ተስፋዬ ቻላ · ልባርከው ጌታዬን ልባርከው

ዘማሪ ፡ ተስፋዬ ፡ ጫላ ርዕስ ፡ ሳልወድህ የወደድከኝ አልበም ፡ ልባርከው ፡ ጌታዬን ፡ ልባርከ ሳልወድህ ፡ የወደድከኝ ፡ ሳልመርጥህ ፡ የመረጥከኝ በከበረው ፡ ደም ፡ ገዝተህ ፡ እንዲያው ፡ ልጅህ ፡ ያረከኝ አበሳዬን ፡ አራከው ፡ ቀንበሬን ፡ ሰባበርከው (ፍቅርህ ፡ ለእኔ ፡ ልዩ ፡ ነው ፡ ስምህን ፡ ላሞጋግሰው) (፪x) ኃጢአተኛ ፡ ሳለሁ ፡ ጽድቅ ፡ የማይገባኝ መርገሜን ፡ ወሰደው ፡ ኢየሱስ ፡ በደሙ ፡ አነጻኝ የከሰሰኝ ፡ ጠላት ፡ እግሬ ፡ ስር ፡ ወደቀ በረሃው ፡ ሕይወቴ ፡ ምንጭን ፡ አፈለቀ አዝ ሳልወድህ ፡ የወደድከኝ... ለዚህ ፡ የሚያበቃ ፡ ጽድቅ ፡ እንኳን ፡ ሳይኖረኝ በሰማዩ ፡ ስፍራ ፡ በቀኙ ፡ እንዲሁ ፡ አከበረኝ ምህረቱ ፡ ብዙ ፡ ይሄ ፡ ታላቅ ፡ ጌታ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ሆናችሁ ፡ በዜማ ፡ አክብሩት ፡ በልልታ አዝ ሳልወድህ ፡ የወደድከኝ... የዕዳ ፡ ጽህፈቴን ፡ በደሙ ፡ ደምስሶ ጠላቴን ፡ በእጄ ፡ እረግጦ ፡ ሰጠኝ ፡ አሳልፎ ጽኑ ፡ ስልጣን ፡ አለኝ ፡ የአምላክ ፡ ልጅ ፡ ሆኛለሁ የፈታኝን ፡ ጌታ ፡ ተፈትቸ ፡ አከብረዋለሁ አዝ ሳልወድህ ፡ የወደድከኝ... ለዚህ ፡ የሚያበቃ ፡ ጽድቅ ፡ እንኳን ሳይኖረኝ በሰማዩ ፡ ስፍራ ፡ በቀኙ ፡ እንዲሁ አከበረኝ ምህረቱ ፡ ብዙ ፡ ይሄ ፡ ታላቅ ፡ ጌታ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ሆናችሁ ፡ በዜማ ፡ አክብሩት ፡ በልልታ አዝ ሳልወድህ ፡ የወደድከኝ... ለዚህ ፡ የሚያበቃ ፡ ጽድቅ ፡ እንኳን ፡ ሳይኖረኝ በሰማዩ ፡ ስፍራ ፡ በቀኙ ፡ እንዲሁ ፡ አከበረኝ ምህረቱ ፡ ብዙ ፡ ይሄ ፡ ታላቅ ፡ ጌታ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ሆናችሁ ፡ በዜማ ፡ አክብሩት ፡ በልልታ አዝ ሳልወድህ ፡ የወደድከኝ...

ተስፋዬ ቻላ · ሁሉም ዘማሪዎች