Gubae

Mesgana Ahahatitle

ተስፋዬ ቻላ · ልባርከው ጌታዬን ልባርከው

Artist Tesfaye Chala ርዕስምሥጋና ፡ አሃሃ አልበም ፡ ልባርከው ፡ ጌታዬን ፡ ልባርከው ገናና ፡ የእኛ ፡ ኢየሱሱ ፡ አቻ ፡ አይገኝለት እንደሞተ ፡ አልቀረም ፡ ከቶ ፡ አለ ፡ በሰማያት ማን ፡ ይቃወመናል ፡ ዛሬስ ፡ በደሙ ፡ ዋጅቶናል ትንሴኤውን ፡ ልናወራ (በገና ፡ አንስተናል) (፪x) (ምሥጋና) (፫x) ለሆነው ፡ ገናና (ዕልልታ) (፫x) ድል ፡ ላረገው ፡ ጌታ ከሰማይ ፡ ሰማያት ፡ ከዙፋኑ ፡ ወርዶ የዕዳውን ፡ ጽህፈት ፡ በደሙ ፡ አስወግዶ ምስኪን ፡ መስሎ ፡ መቶ ፡ ዲያብሎስን ፡ ቀጣ በጨለማ ፡ ላሉ ፡ አዲስ ፡ ፀሐይ ፡ ወጣ አዝ ገናና ፡ የእኛ ፡ እየሱስ... ጐስቋላና ፡ ድሃ ፡ ምስኪን ፡ የህማም ፡ ሰው ባየነውም ፡ ጊዜ ፡ ደም ፡ ግባት ፡ የሌለው ፍቅር ፡ ኃይሉ ፡ ሆነች ፡ ድካሙ ፡ በረታ ማንም ፡ ሳያግዘው ፡ ዲያብሎስን ፡ መታ አዝ ገናና ፡ የእኛ ፡ ኢየሱስ... የጣር ፡ የሰቆቃው ፡ ጩኸቱ ፡ ሲሰማ መከራው ፡ በዝቶበት ፡ ቢመስልም ፡ ደካማ ምድር ፡ አልቻለችም ፡ ሞትን ፡ ፈነቀለ ተስፋ ፡ ለቆረጡ ፡ አዲስ ፡ ዘር ፡ በቀለ አዝ ገናና ፡ የእኛ ፡ ኢየሱስ... ስሙም ፡ ድንቅ ፡ መካር ፡ የሰላም ፡ አለቃ ሞትና ፡ ርግማንም ፡ ስቃዩ ፡ አበቃ ገናና ፡ ገናና ፡ ገናና ፡ ነው ፡ አሱ በሆታ ፡ በልልታ ፡ ስሙን ፡ አሞግሱ አዝ ገናና ፡ የስኛ ፡ ኢየሱስ...

ተስፋዬ ቻላ · ሁሉም ዘማሪዎች