Gubae

Keber Lehonen Gieta

ተስፋዬ ቻላ · ልባርከው ጌታዬን ልባርከው

አዝ ክበር ፡ የሆነን ፡ ጌታ ሞገስ ፡ የሆነን ፡ ጌታ ብቃት ፡ የሆነን ፡ ጌታ በጉድለታችን ፡ ፈንታ ክንዱን ፡ በዘመናችን ፡ በዓይናችን ፡ አይተነዋል መልካም ፡ እረኛ ፡ ኢየሱስ ፡ እስከዛሬ ፡ ረድቶናል በዘመን ፡ በአመታት ፡ መሃል የሚገዳደረው ፡ የታል ብቻውን ፡ ድንቅ ፡ እየሰራ የሚኖር ፡ እንደተፈራ ለእኛም ፡ ይሄው ፡ ሞገስ ፡ ሆነን ባሕሩን ፡ ከፍሎ ፡ አሻገረን ችግራችንን ፡ እረሳነው ፡ በኢየሱስ ፡ ስንቱን ፡ አለፍን አዝ ክበር ፡ የሆነን ፡ ጌታ... ስንቱን ፡ ተሻገርን ፡ አለፍን በምሥጋና ፡ ሆ ፡ እያልን ስንቱስ ፡ ከእግራችን ፡ ወደቀ በኢየሱስ ፡ እየደቀቀ ዘመን ፡ ሲያልፍ ፡ ዘመን ፡ ሲተካ ፍሬያችን ፡ አብቦ ፡ ፈካ የረገጥነውን ፡ ወረስን እለት ፡ እለት ፡ አማረብን አዝ ክበር ፡ የሆነን ፡ ጌታ... በምድረ ፡ በዳ ፡ በረሃ ፡ የሚያረካ ፡ ውኃ ሆነን አልሰለቸን ፡ የእኛ ፡ ጌታ ፡ እንደቃሉ ፡ ተለመነን በመከራ ፡ ቀን ፡ ሰቀቀን ፡ ተማምነን ፡ ስሙን ፡ ስንጠራ ደረሰልን ፡ በሰአቱ ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ የሚያኮራ አዝ ክበር ፡ የሆነን ፡ ጌታ... ሸንጐ ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ሲማከር ዲያብሎስ ፡ ሊያጠፋን ፡ ሲጥር ማነው ፡ ደርሶ ፡ የታደገን በመከራ ፡ መርከብ ፡ ሆነን ታሪክ ፡ ይናገር ፡ ብዙ ፡ ነው ብዙ ፡ ነው ፡ እኛስ ፡ ያለፍነው ከእግራችን ፡ ስር ፡ ወድቆ ፡ ጠላት ጭንቅላቱን ፡ እረገጥነው አዝ ክበር ፡ የሆነን ፡ ጌታ...

ተስፋዬ ቻላ · ሁሉም ዘማሪዎች