Kante Gara
ተስፋዬ ቻላ · ወጥመዱ ተሰብሮ አመለጥኩኝ
ዘማሪ ፡ ተስፋዬ ፡ ጫላ ርዕስ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ አልበም ፡ ወጥመዱ ፡ ተሰብሮ አመለጥኩኝ አዝ ከአንተ ፡ ጋራ (፫x) ኢየሱስ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ከአንተ ፡ ጋራ (፫x) ውዴ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ሸለቆው ፡ በውኃ ፡ ይሞላል ፡ የማይቻለው ፡ ይቻላል እኔ ፡ አይቻለሁ ፡ ስትሰራ ፡ አላፈርኩም ፡ ከአንተ ፡ ጋራ (፪x) ሸለቆው ፡ በውኃ ፡ ይሞላል ፡ የማይቻለው ፡ ይቻላል እኔ ፡ አይቻለሁ ፡ ስትሰራ ፡ አሸነፍኩኝ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ (፪x) የማይሸከሙት ፡ ለሰው ፡ የማይነግሩት ወይ ፡ በሆድ ፡ ደብቀው ፡ የማያባብሉት ሥጋት ፡ የማይገፋው ፡ የዚህ ፡ ምድር ፡ ጣጣ ትንሹን ፡ ሲሸኙት ፡ ትልቁ ፡ ሲመጣ አለፍኩት ፡ ሁሉንም ፡ ውዴ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ አቀበት ፡ ቁልቁለት ፡ ሜዳና ፡ ተራራ ስወድቅ ፡ ያረሳኸኝ ፡ ስደክም ፡ ያነሳኸኝ በዚች ፡ አጭር ፡ ዕድሜ ፡ ስንቱን ፡ አሳለፍከኝ አዝ ከአንተ ፡ ጋራ (፫x) ኢየሱስ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ከአንተ ፡ ጋራ (፫x) ውዴ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ሸለቆው ፡ በውኃ ፡ ይሞላል ፡ የማይቻለው ፡ ይቻላል እኔ ፡ አይቻለሁ ፡ ስትሰራ ፡ አላፈርኩም ፡ ከአንተ ፡ ጋራ (፪x) ሸለቆው ፡ በውኃ ፡ ይሞላል ፡ የማይቻለው ፡ ይቻላል እኔ ፡ አይቻለሁ ፡ ስትሰራ ፡ አሸነፍኩኝ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ (፪x) የዚህ ፡ ዓለም ፡ ክፋት ፡ መውረድና ፡ መውጣት ነፍሴን ፡ ቀንና ፡ ሌሊት ፡ እያንከራተታት አቅም ፡ አጣሁ ፡ ብዬ ፡ ጉልበቴ ፡ ሲከዳኝ ስጮህ ፡ ሳለቃቅስ ፡ ፈልጌ ፡ የሚረዳኝ በእኩለ ፡ ሌሊት ፡ የመጣኸው ፡ ጌታ ደግመህ ፡ አስታጠከኝ ፡ ጉልበቴ ፡ ሲፈታ እቀኝልሃለሁ ፡ ክብር ፡ ይሁንልህ በምንም ፡ በማንም ፡ እኔስ ፡ አልለውጥህ አዝ ከአንተ ፡ ጋራ (፫x) ኢየሱስ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ከአንተ ፡ ጋራ (፫x) ውዴ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ሸለቆው ፡ በውኃ ፡ ይሞላል ፡ የማይቻለው ፡ ይቻላል እኔ ፡ አይቻለሁ ፡ ስትሰራ ፡ አላፈርኩም ፡ ከአንተ ፡ ጋራ (፪x) ሸለቆው ፡ በውኃ ፡ ይሞላል ፡ የማይቻለው ፡ ይቻላል እኔ ፡ አይቻለሁ ፡ ስትሰራ ፡ አሸነፍኩኝ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ (፪x) ከእንግዲህስ ፡ አይሆንም ፡ ብዬ ፡ የዘጋሁት አምርሬ ፡ አልቅሼ ፡ አፈር ፡ ያለበስኩት ተስፋ ፡ የሌለበት ፡ የሞተው ፡ ነገሬ ልረሳው ፡ ስሞክር ፡ በጊዜ ፡ ቀብሬ አንተ ፡ ከሰማያት ፡ ወርደህ ፡ ስታልፍበት በሞት ፡ ፈንታ ፡ ሕይወት ፡ ብለህ ፡ ስታዝበት የሞተው ፡ ተነስቶ ፡ ሲሄድ ፡ አይቻለሁ ለተዓምራትህ ፡ ምስክር ፡ ሆናለሁ አዝ ከአንተ ፡ ጋራ (፫x) ውዴ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ከአንተ ፡ ጋራ (፫x) ኢየሱስ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ሸለቆው ፡ በውኃ ፡ ይሞላል ፡ የማይቻለው ፡ ይቻላል እኔ ፡ አይቻለሁ ፡ ስትሰራ ፡ አላፈርኩም ፡ ከአንተ ፡ ጋራ (፪x) ሸለቆው ፡ በውኃ ፡ ይሞላል ፡ የማይቻለው ፡ ይቻላል እኔ ፡ አይቻለሁ ፡ ስትሰራ ፡ አሸነፍኩኝ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ (፪x)

