Bechawen Teamer Yemisera
ተስፋዬ ቻላ · ልባርከው ጌታዬን ልባርከው
ዘማሪ ፡ ተስፋዬ ፡ ጫላ ርዕስ ፡ ብቻውን ፡ ተዓምር ፡ የሚሰራ አልበም ፡ ልባርከው ፡ ጌታዬን ፡ ልባርከው (ብቻውን ፡ ተዓምር ፡ የሚያደርግ ፡ ችግረኛን ፡ የሚታደግ እንቆቅልሽ ፡ የሚፈታ ፡ ኢየሱስ ፡ የኛ ፡ ጌታ) (፪x) ጠላት ፡ ሲሽቀዳደም ፡ ሊመታን ፡ በጡጫ ቅጥሩን ፡ ሰበረልን ፡ ሆነልን ፡ ማምለጫ እንናገር ፡ ብንል ፡ ብዙ ፡ እናወራለን በዝች ፡ አጭር ፡ እድሜ ፡ ምረቱን ፡ ስላየን በዝች ፡ አጭር ፡ ዘመን ፡ ማዳኑን ፡ ስላየን አዝ ብቻውን ፡ ተዓምር... ኃጢአታችን ፡ በዝቶ ፡ ስንባዝን ፡ በዓለም ሕይወት ፡ ሆነን ፡ የሱስ ፡ ሊያኖረን ፡ ዘለዓለም ምን ፡ እንመልሳለን ፡ ምሥጋና ፡ ሌላ በጭንቃችን ፡ ስዓት ፡ ለሆነን ፡ ከለላ (በጭንቃችን ፡ ስዓት ፡ ለሆነን ፡ ከለላ) አዝ ብቻውን ፡ ተዓምር... የአናብስትን ፡ አፍ ፡ ጥርስ ፡ እየሰበረ ከክብር ፡ ወደ ፡ ክብር ፡ እያሸጋገረ በደመናው ፡ አምድ ፡ ዘወትር ፡ ይመራናል ከኢየሱስ ፡ ጋር ፡ ሆነን ፡ አረ ፡ ምን ፡ ጐሎናል ከኢየሱስ ፡ ጋር ፡ ሆነን ፡ አረ ፡ ምን ፡ ጐሎናል አዝ ብቻውን ፡ ተዓምር... ጠላት ፡ ሲሽቀዳደም ፡ ሊመታን ፡ በጡጫ ቅጥሩን ፡ ሰበረልን ፡ ሆነልን ፡ ማምለጫ እንናገር ፡ ብንል ፡ ብዙ ፡ እናወራለን በዝች ፡ አጭር ፡ እድሜ ፡ ምረቱን ፡ ስላየን በዝች ፡ አጭር ፡ ዘመን ፡ ማዳኑን ፡ ስላየን አዝ ብቻውን ፡ ተዓምር...

