ባማረ ቅኔ
Bamare Qenie
ተስፋዬ ቻላ · ባማረ ቅኔ
ዘማሪ ፡ ተስፋዬ ፡ ጫላ ርዕስ ፡ ባማረ ፡ ቅኔ አዝ ባማረ ፡ ቅኔ ፡ ለኢየሱስ ፡ ምሥጋና ቃሉን ፡ የሚያደርግ ፡ ድንቅ ፡ አምላክ ፡ ነውና ደመናም ፡ ባላይ ፡ ሸለቆው ፡ ይሞላል ሰው ፡ የማይችለው ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ይቻላል እኔስ ፡ ተስፋ ፡ አልቆርጥም ፡ ፍፁም ፡ አላፍርም ፡ ባዳነኝ ፡ ጌታ አይቻለሁና ፡ በዐይኔ ፡ ያስጨነቀኝን ፡ ሲመታ ነገር ፡ ባይሞላ ፡ ባይሳካ ፡ ኢየሱስ ፡ ምን ፡ ይሳነዋል ከሞተው ፡ አንበሳ ፡ ሆድ ፡ ውስጥ ፡ ጣፋጭ ፡ ጣፋጭ ፡ ማር ፡ ያወጣል (፪x) አዝ ባማረ ፡ ቅኔ ፡ ለኢየሱስ ፡ ምሥጋና ቃሉን ፡ የሚያደርግ ፡ ድንቅ ፡ አምላክ ፡ ነውና ደመናም ፡ ባላይ ፡ ሸለቆው ፡ ይሞላል ሰው ፡ የማይችለው ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ይቻላል ለምን ፡ ልጐሳቆል ፡ ልዘን ፡ ለምንስ ፡ ልቆዝም ፡ በእንባ ተዓምር ፡ ያስለመደኝ ፡ አምላክ ፡ መቼ ፡ ክንዱ ፡ ደከመና በታሰርኩበት ፡ ወህኒ ፡ ውስጥ ፡ ሆ ፡ እያልኩኝ ፡ እዘምራለሁ የጠላቶቼን ፡ ደጅ ፡ በእምነት ፡ በዝማሬ ፡ አፈርሳለሁ (፪x) አዝ ባማረ ፡ ቅኔ ፡ ለኢየሱስ ፡ ምሥጋና ቃሉን ፡ የሚያደርግ ፡ ድንቅ ፡ አምላክ ፡ ነውና ደመናም ፡ ባላይ ፡ ሸለቆው ፡ ይሞላል ሰው ፡ የማይችለው ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ይቻላል ውድቀቴን ፡ ጠላቴ ፡ ሰምቶ ፡ ከበሮ ፡ ተይዞ ፡ ሲጨፈር አምላኩ ፡ ጥሎታል ፡ ዛሬስ ፡ ተብሎ ፡ አዋጅ ፡ ሲነገር ሰው ፡ የማይጥል ፡ ጌታ ፡ አምላኬ ፡ ኃያል ፡ ክንዱን ፡ ሲዘረጋ ጠላቶቼ ፡ ሁሉ ፡ አለቁ በአንዲት ፡ የአህያ ፡ መንጋጋ (፪x) አዝ ባማረ ፡ ቅኔ ፡ ለኢየሱስ ፡ ምሥጋና ቃሉን ፡ የሚያደርግ ፡ ድንቅ ፡ አምላክ ፡ ነውና ደመናም ፡ ባላይ ፡ ሸለቆው ፡ ይሞላል ሰው ፡ የማይችለው ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ይቻላል ሰላሙን ፡ ሞልቶ ፡ አባቴ ፡ በመስቀሉ ፡ ስራ ፡ አሳረፈኝ ወደ ፡ ክብሩ ፡ ልጁም ፡ መንግሥት ፡ በታላቅ ፡ ፍቅሩ ፡ አፈለሰኝ ልጁን ፡ ለእኔ ፡ የሰጠ ፡ አምላክ ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ ምን ፡ ይሳነዋል ባዶ ፡ ሸለቆዬ ፡ ሞልቶ ፡ ተርፎ ፡ ለአገር ፡ ሁሉ ፡ ይፈሳል (፪x) አዝ ባማረ ፡ ቅኔ ፡ ለኢየሱስ ፡ ምሥጋና ቃሉን ፡ የሚያደርግ ፡ ድንቅ ፡ አምላክ ፡ ነውና ደመናም ፡ ባላይ ፡ ሸለቆው ፡ ይሞላል ሰው ፡ የማይችለው ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ይቻላል

