Aderegelegn Teamer
ተስፋዬ ቻላ · የበላይ ነህ ጌታ
እንዳለፈ ፡ ውኃ ፡ መከራዬን ፡ አስረሳኝ በጠላቶቼ ፡ ፊት ፡ እራሴን ፡ በዘይት ፡ ቀባ ኧረ ፡ እንዴት ፡ ይበዛል ፡ ሌት ፡ ተቀን ፡ ባከብረው ማንም ፡ የማይመስለው ፡ ወዳጅ ፡ አግኝቻለሁ (፬x) አሃሃ ፡ የጠላቴ ፡ ዛቻ ፡ አሃሃ ፡ አይ ፡ ማስፈራራቱ አሃሃ ፡ ከንቱ ፡ ሆኖ ፡ ቀረ ፡ አሃሃ ፡ ቀደመች ፡ ምህረቱ አሃሃ ፡ ሌሊት ፡ በእሳት ፡ አምድ ፡ አሃሃ ፡ በደመና ፡ መራኝ አሃሃ ፡ እረ ፡ ማነው ፡ ከልካይ ፡ አምላኬ ፡ ከረዳኝ እረ ፡ ማነው ፡ ከልካይ ፡ ኤልሻዳይ ፡ ከረዳኝ አዝ አደረገልኝ ፡ ተአምር ፡ አደረገልኝ (፪x) ተራራዬን ፡ ናደው ፡ ናደው ፡ ሸለቆዬን ፡ ሞላ ፡ ሃሃ ባሕሩን ፡ ከፈለው ፡ ኦሆሆ ፡ መንገዴን ፡ አቀና (፪x) ዘይት ፡ ከማሰሮ ፡ ከማድጋው ፡ አልቆ ተስፋዬ ፡ ተሰብሮ ፡ ተሰባብሮ ፡ ደቆ ስሙን ፡ ተጣርቼ ፡ የልቤን ፡ ስነግረው እፌን ፡ ሞልቶ ፡ በሳቅ ፡ ሕይወቴን ፡ አዳነው የአምናው ፡ ችግር ፡ ሄደ ፡ ማድጋው ፡ ሙሉ ፡ ነው ከራሴ ፡ ተርፌ ፡ አለኝ ፡ የምሰጠው የታምራት ፡ አምላክ ፡ ተአምር ፡ አድርጐልኛል ፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ ይስማው ፡ ነገር ፡ ተገልብጧል አዝ አደረገልኝ ፡ ተአምር ፡ አደረገልኝ (፪x) ተራራዬን ፡ ናደው ፡ ናደው ፡ ሸለቆዬን ፡ ሞላ ፡ አሃሃ ባሕሩን ፡ ከፈለው ፡ ኦሆሆ ፡ መንገዴን ፡ አቀና (፪x) አሃሃ ፡ አዲስ ፡ ቅኔ ፡ ላምጣ ፡ አሃሃ ፡ ላክብረው ፡ ሳልቆጥብ አሃሃ ፡ እግሮቼም ፡ ይዝለሉ ፡ በፊቱ ፡ ላሸብሽብ አሃሃ ፡ ክብሬን ፡ ብጥልለት ፡ አሃሃ ፡ የሚንቀኝ ፡ ማነው አሃሃ ፡ ያደረገልኝን ፡ እኔ ፡ ነኝ ፡ የማውቀው አሃሃ ፡ የተሰራልኝን ፡ እኔ ፡ ነኝ ፡ የማውቀው ሰማይ ፡ ጥርት ፡ አለ ፡ ደመናውም ፡ ጠፋ የችግሩ ፡ ብርታት ፡ ፊቴን ፡ ለቆ ፡ ጠፋ የነበረው ፡ ሄደ ፡ ያለውም ፡ አለቀ ውኃ ፡ ሳይኖርበት ፡ ሸለቆው ፡ ደረቀ ደመናም ፡ ሳይታይ ፡ ንፋስም ፡ ሳይነፍስ ዝናባትን ፡ አዞ ፡ ምድርን ፡ ሲያረሰርስ የጠላቴን ፡ እቅድ ፡ እያፈረሰልኝ ድል ፡ በድል ፡ ላይ ፡ ለመድኩ ፡ ድንቅ ፡ አደረገልኝ አዝ አደረገልኝ ፡ ተዐምር ፡ አደረገልኝ (፪x) ተራራዬን ፡ ናደው ፡ ናደው ፡ ኦሆሆ ፡ ሸለቆዬን ፡ ሞላ ባሕሩን ፡ ከፈለው ፡ ኦሆሆ ፡ መንገዴን ፡ አቀና (፪x)

