Gubae

Yehulie

ተከስተ ጌትነት · መጀመሪያ

ፍቅር ፡ የጎደለበት ፡ ባግባቡ ፡ እንኳን ፡ ያልኖረ አይዞ ፡ ባይ ፡ ወገን ፡ የሌለው ፡ ብቸኛ ፡ የነበረ ያለበት ፡ ድረስ ፡ መተህ ፡ ወድሃለው ፡ ስትለው ልቡን ፡ ከማፍሰስ ፡ በቀር ፡ ምንስ ፡ ሌላ ፡ አማራጭ ፡ አለው መመኪያዬ (X3) አንተው ፡ ነህ ፡ ጌታዬ (X2) ላፍታ ፡ ሳትለየኝ ፡ በድካም ፡ ሆነ ፡ በብርታት ስንት ፡ ግዜ ፡ ረዳኀኝ ፡ ባሳለፍኳቸው ፡ አመታት ልቤን ፡ ኩራት ፡ አለው ፡ ዘንድሮም ፡ ተመካብህ የማትለዋወጥ ፡ የህይወቴ ፡ ዋስትና ፡ ነህ የሁሌ ፡ ነህ ፡ የሁሌ ፡ አምላኬ ፡ ነህ ፡ የሁሌ አፍቃሪ ፡ ወረት ፡ የለብህ ፡ ውዴ ፡ ልበልህ ፡ እንዳመሌ ማይዘነጋ ፡ ነው ፡ አይጠፋም ፡ ከሃሳቤ ሁሌ ፡ ድቅን ፡ ይልብኛል ፡ ፍቅርህ ፡ ታትሟል ፡ በልቤ ብዙ ፡ ወጀብ ፡ አልፎ ፡ ትኩሳቱ ፡ እንደው ፡ አይበርድም ዛሬም ፡ አንተኑ ፡ ይለኛል ፡ አይለውጥህም ፡ በማንም የሁሌ ፡ ነህ ፡ የሁሌ ፡ አምላኬ ፡ ነህ ፡ የሁሌ አፍቃሪ ፡ ወረት ፡ የለብህ ፡ ውዴ ፡ ልበልህ ፡ እንዳመሌ ማይዘነጋ ፡ ነው ፡ አይጠፋም ፡ ከሃሳቤ ሁሌ ፡ ድቅን ፡ ይልብኛል ፡ ፍቅርህ ፡ ታትሟል ፡ በልቤ ብዙ ፡ ወጀብ ፡ አልፎ ፡ ትኩሳቱ ፡ እንደው ፡ አይበርድም ዛሬም ፡ አንተኑ ፡ ይለኛል ፡ አይለውጥህም ፡ በማንም የሁሌ ፡ ነህ ፡ የሁሌ ፡ አምላኬ ፡ ነህ ፡ የሁሌ አፍቃሪ ፡ ወረት ፡ የለብህ ፡ ውዴ ፡ ልበልህ ፡ እንዳመሌ

ተከስተ ጌትነት · ሁሉም ዘማሪዎች