ምክንያቴ ብዙ ነው
Mekniyatie Bezu New
ተከስተ ጌትነት · ምክንያቴ ብዙ ነው
ዘማሪ ፡ ተከስተ ፡ ጌትነት ርዕስ ፡ ምክንያቴ ፡ ብዙ ፡ ነው Volume 2 አንደበቴ ፡ ከምስጋና ፡ በቀር ፡ ሌላ ፡ አያውቅም ይዘምራል ፡ ላንተ ፡ ክብር ፡ ሰለቸኝ ፡ አይልም ደግነትህ ፡ በሕይወቴ ፡ እጅግ ፡ ስለበዛ ፡ አሳጣኸኝ ፡ ከቶ ፡ ምለው ፡ ከምሥጋና ፡ ሌላ (፪x) አዝ ምክንያቴ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ብዙ አጥንቶቼም ፡ በርቱ ፡ ለአምላኬ ፡ ተገዙ ነፍሴ ፡ ሆይ ፡ አክብሪው ፡ ከሞት ፡ ያዳነሽን ዝም ፡ አትበይ ፡ ተነሽ ፡ አመስግኝ ፡ ጌታሽን (፪x) ከቶ ፡ አልሻም ፡ በዘመኔ ፡ ካንተ ፡ ሌላ ፡ ለኔ ቆርጫለሁ ፡ ላልለይህ ፡ ኢየሱስ መድህኔ ብቻ ፡ አንተ ፡ ክበር ፡ እንጂ ፡ ይሁን ፡ ደስ ፡ እንዳለህ አልሰለችም ፡ ሁልጊዜ ፡ ጌታዬ ፡ ባከብርህ (፪x) አዝ ምክንያቴ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ብዙ አጥንቶቼም ፡ በርቱ ፡ ለአምላኬ ፡ ተገዙ ነፍሴ ፡ ሆይ ፡ አክብሪው ፡ ከሞት ፡ ያዳነሽን ዝም ፡ አትበይ ፡ ተነሽ ፡ አመስግኝ ፡ ጌታሽን (፪x) ልማድህ ፡ ነው ፡ ከፍ ፡ ማድረግ ፡ ከብረህ ፡ የምታከብር ትቢያ ፡ አራግፈህ ፡ መሸላለም ፡ ማብቃት ፡ ለቁም ፡ ነገር ስንቱ ፡ አረፈ ፡ እፎይ ፡ አለ ፡ ወዳንተ ፡ ሲጠጋ አመለጠ ፡ ባንተ ፡ ጉልበት ፡ ከጠላት ፡ መንጋጋ (፪x) አዝ ምክንያቴ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ብዙ አጥንቶቼም ፡ በርቱ ፡ ለአምላኬ ፡ ተገዙ ነፍሴ ፡ ሆይ ፡ አክብሪው ፡ ከሞት ፡ ያዳነሽን ዝም ፡ አትበይ ፡ ተነሽ ፡ አመስግኝ ፡ ጌታሽን (፪x) በምስጋና ፡ ላይ ፡ ምስጋና ፡ ገና ፡ አበዛለሁ ተባረክ ፡ ብዬ ፡ ሁልጊዜ ፡ መቼ ፡ እጠግባለሁ (፪x) በዝማሬ ፡ ላይ ፡ ዝማሬ ፡ ገና ፡ አበዛለሁ ተባረክ ፡ ብዬ ፡ ሁልጊዜ Bold textመቼ ፡ እጠግባለሁ (፪x) Bold text

