ኩራት ኩራት አለኝ
Kurat Kurat Alegn
ተከስተ ጌትነት · Singles
ብርቱ ፡ ተብሎ ፡ ታምኖበት ፡ ልብም ፡ በእርሱ ፡ ላይ ፡ ተጥሎ አለልኝ ፡ ለእኔ ፡ እያለ ፡ መኖር ፡ ሲመኝ ፡ ተዘልሎ የተደገፈው ፡ ሸንበቆ ፡ መሆኑን ፡ እንዲያው ፡ ሳያውቀው ድንገት ፡ ተሰብሮ ፡ ወደቀ ፡ የዚያ ፡ ሰው ፡ መተማመኛው አኔማ/እኔ ፡ ግን ፡ በላዬ ፡ ላይ ፡ ንጉሴን ፡ ሾሜያለሁ አልፈራ ፡ አልደነግጥ ፡ በክንዱ ፡ እኮራለሁ (፪x) ኩራት ፡ ኩራት ፡ አለኝ ፡ ብኮራስ ፡ ምናለ እመካለሁ ፡ እኔስ ፡ ብመካ ፡ ምናለ አንበሳው ፡ ኢየሱስ ፡ የእኔ ፡ ሆኖ ፡ የለ ኃይለኛው ፡ ኢየሱስ ፡ ቤቴን ፡ ሞልቶት ፡ የለ ኃይለኛው ፡ ኢየሱስ ፡ የእኔ ፡ ሆኖ ፡ የለ ወዳጄ ፡ ኢየሱስ ፡ ቤቴን ፡ ሞልቶት ፡ የለ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ከቶ ፡ የለምና በሰማይ ፡ በምድር ፡ አልተገኘምና ይብዛልህ ፡ ዛሬም ፡ ምሥጋና ይብዛልህ ፡ ነገም ፡ ምሥጋና (፪x) ዓይኔ ፡ አረፈብህ ፡ ወዳጄ ፡ በምንም ፡ የማትረታ ወረት ፡ አታውቅም ፡ እንደሰው ፡ በጐ ፡ ነህ ፡ ሁሌ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ዘመናት ፡ ሲፈራረቁ ፡ አልተቀየረም ፡ መውደድህ ሁሉን ፡ በጆችህ ፡ ይዘሃል ፡ ታስመካለህ ፡ ቢመኩብህ በልቤ ፡ ሾሜሃለሁ ፡ ከፍ ፡ ብለህ ፡ ደምቀህ ፡ ታይ እንዳንተ ፡ የለምና ፡ በምድር ፡ በሰማይ (፪x) ኩራት ፡ ኩራት ፡ አለኝ ፡ ብኮራስ ፡ ምናለ እመካለሁ ፡ እኔስ ፡ ብመካ ፡ ምናለ አንበሳው ፡ ኢየሱስ ፡ የእኔ ፡ ሆኖ ፡ የለ ኃይለኛው ፡ ኢየሱስ ፡ ቤቴን ፡ ሞልቶት ፡ የለ ኃይለኛው ፡ ኢየሱስ ፡ የእኔ ፡ ሆኖ ፡ የለ ወዳጄ ፡ ኢየሱስ ፡ ቤቴን ፡ ሞልቶት ፡ የለ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ከቶ ፡ የለምና በሰማይ ፡ በምድር ፡ አልተገኘምና ይብዛልህ ፡ ዛሬም ፡ ምሥጋና ይብዛልህ ፡ ነገም ፡ ምሥጋና (፪x) በመከራ ፡ ቀን ፡ ቢጠሩት ፡ አለሁኝ ፡ የሚል ፡ ልብ ፡ ሞልቶ ግራ ፡ ለገባው ፡ መጠጊያ ፡ ሚደግፍ ፡ እጁን ፡ ዘርግቶ መተማመኛ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ተፈትኖ ፡ አልፏል ፡ በብ ደጋግ ፡ እጆቹን ፡ አይተናል ፡ ደካማዎቹን ፡ ሲያግዙ አለልኝ ፡ ይሄ ፡ ጌታ ፡ የማይጥል ፡ የማይከዳ ሰባራን ፡ የሚጠግን ፡ ወዳጅ ፡ ነው ፡ በምድረበዳ (፪x) ኩራት ፡ ኩራት ፡ አለኝ ፡ ብኮራስ ፡ ምናለ እመካለሁ ፡ እኔስ ፡ ብመካ ፡ ምናለ አንበሳው ፡ ኢየሱስ ፡ የእኔ ፡ ሆኖ ፡ የለ ኃይለኛው ፡ ኢየሱስ ፡ ቤቴን ፡ ሞልቶት ፡ የለ ኃይለኛው ፡ ኢየሱስ ፡ የእኔ ፡ ሆኖ ፡ የለ ወዳጄ ፡ ኢየሱስ ፡ ቤቴን ፡ ሞልቶት ፡ የለ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ከቶ ፡ የለምና በሰማይ ፡ በምድር ፡ አልተገኘምና ይብዛልህ ፡ ዛሬም ፡ ምሥጋና ይብዛልህ ፡ ነገም ፡ ምሥጋና (፰x)

