ከስም ሁሉ በላይ
Kesem Hulu Belay
ተከስተ ጌትነት · Negestat Biqeyeru
አዝ፦ (ማን ፡ ልበለው ፡ ጌታን ማን ፡ ልበለው ፡ ኢየሱሴን) X፪ (ከስም ፡ ሁሉ ፡ በላይ ፡ ስም ፡ አለው ለእርሱ ፡ ማይገዛ ፡ እስኪ ፡ ማነው ሁሉን ፡ በፈቃዱ ፡ የሚያደርገው አምላኬ ፡ የጌቶች ፡ ጌታ ፡ ነው) X2 (ኧረ ፡ ስንቱን ፡ ስንቱን ፡ አለፍኩኝ በምህረቱ ፡ ብዛት ፡ ደግፎኝ ቢነሳ ፡ ቢነገር ፡ ውለታው አያልቅም ፡ ካይምሮ ፡ በላይ ፡ ነው) ፡ X2 አዝ እንካ ፡ ተንሰራፋ ፡ በልቤ ፡ ዙፋን ፡ ላይ ፡ ምን ፡ እኔነት ፡ አለኝ ፡ ሁሉ ፡ ያንተ ፡ አይደል ፡ ወይ በተቀደሰው ፡ ተራራዬ ፡ ላይ ፡ አንተው ፡ ድመቅበት ፡ ሳይኖርህ ፡ ከልካይ በሁሉ ፡ ላይ ፡ ሾምኩህ ፡ በሁሉ ፡ ነገር ፡ ላይ ሁሉም ፡ ይወቅልኝ ፡ (መሆንክን ፡ የበላይ) X2 አንደበቱን ፡ ከፍቶ ፡ ፍጥረት ፡ ያመስግንህ በሰማይ ፡ በምድር ፡ (አቻ ፡ አልተገኘልህ) X2 አዝ (ያፍህ ፡ ቃል ፡ ውድዬ ፡ ጣፋጭ ፡ ነው ማለዳ ፡ ማለዳ ፡ አዲስ ፡ ነው ሳላነሳህ ፡ ውዬ ፡ አላድርም ከአንተ ፡ ውጪ ፡ እርካታ ፡ የለኝም) X2 አዝ

