Gubae

Metahugn

ታጋይ ወልደማርያም · Singles

ይኸው ፡ ደስ ፡ እያለኝ ፡ መጣሁኝ ፡ ላመልክህ ምስጋና ፡ ይዤ ፣ አምልኮ ፡ ይዤ ፣ መስዋዕቴን ፡ ይዤ ይኸው ፡ ዙፋንህ ፡ ስር ፡ መጣሁኝ ፡ ላመልክህ ምስጋና ፡ ይዤ ፣ አምልኮ ፡ ይዤ ፣ መስዋዕቴን ፡ ይዤ አንተ ፡ ቅዱስ ፡ ነህ ፡ ቅዱስ (፫x) የማመልክህ (ቅዱስ ፡ ነህ ፡ ቅዱስ) ምስክር ነኝ (ቅዱስ ፡ ነህ ፡ ቅዱስ) ልከተልህ (ቅዱስ ፡ ነህ ፡ ቅዱስ) የጠራኸኝ (ቅዱስ ፡ ነህ ፡ ቅዱስ) ከጫፍ ፡ እስከ ፡ ጫፍ ከአጥናፍ ፡ እስከ ፡ አጥናፍ አምላክ ፡ ነኝ ፡ ባዩ ፡ ሁሉ ፡ ይሰለፍ ሰምቶ ፡ በእሳት ፡ የሚመልሰው የኤልያስ ፡ አምላክ ፡ እርሱ ፡ አምላክ ፡ ነው የልቤ ፡ ጉልበት ፡ ተንበረከከ ፡ ይህንን ፡ አውቆ ክብር ፡ ሚጋራ ፡ ደባሉን ፡ ሁሉ ፡ በእርሱ ፡ አርቆ የእድሜዬም ፡ አፍላ ፡ ሽምግልናዬም ፡ ለእርሱ ፡ ይገዛል ወዶ ፡ እና ፡ ፈቅዶ ፡ መላው ፡ እኔነቴ ፡ ክብር ፡ ይሰጣል (፪x) ይኸው ፡ ደስ ፡ እያለኝ ፡ መጣሁኝ ፡ ላመልክህ ምስጋና ፡ ይዤ ፣ አምልኮ ፡ ይዤ ፣ መስዋዕቴን ፡ ይዤ ይኸው ፡ ዙፋንህ ፡ ስር ፡ መጣሁኝ ፡ ላመልክህ ምስጋና ፡ ይዤ ፣ አምልኮ ፡ ይዤ ፣ መስዋዕቴን ፡ ይዤ አንተ ፡ ቅዱስ ፡ ነህ ፡ ቅዱስ (፫x) የማመልክህ (ቅዱስ ፡ ነህ ፡ ቅዱስ) ምስክር ነኝ (ቅዱስ ፡ ነህ ፡ ቅዱስ) ልከተልህ (ቅዱስ ፡ ነህ ፡ ቅዱስ) የጠራኸኝ (ቅዱስ ፡ ነህ ፡ ቅዱስ) የእድሜው ፡ ልኩ ፡ ከእስከ ፡ የለው አልፋ ፡ ኦሜጋ ፡ እየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው ጠቢብ ፡ አዋቂው ፡ ቢሰበሰብም በዚህች ፡ አይምሮው ፡ እርሱ ፡ አይለካም የልቤ ፡ ጉልበት ፡ ተንበረከከ ፡ ይህንን ፡ አውቆ ክብር ፡ ሚጋራ ፡ ደባሉን ፡ ሁሉ ፡ በእርሱ ፡ አርቆ የእድሜዬም ፡ አፍላ ፡ ሽምግልናዬም ፡ ለእርሱ ፡ ይገዛል ወዶ ፡ እና ፡ ፈቅዶ ፡ መላው ፡ እኔነቴ ፡ ክብር ፡ ይሰጣል (፪x)

ታጋይ ወልደማርያም · ሁሉም ዘማሪዎች