ይገርማል
Yegermal
ሰለሞን ይርጋ · ይገርማል · 2005
ምንም ፡ ክፍያ ፡ አልከፈልኩም ከላይ ፡ ወደታችም ፡ አላልኩም በጓደኛም ፡ ዘመድ ፡ አልመጣሁም ጌታን ፡ ለማግኘት ፡ አልደከምኩም በፍቅር ፡ ቃሉ ፡ ሲናገረኝ እወድሃልሁ ፡ ብሎ ፡ ሲለኝ እጅግ ፡ ተገረምኩ ፡ ተደነቅኩ እንዲህ ፡ ያለ ፡ ሰው ፡ ማነው ፡ አልኩ ያለ ፡ የነበረ ፡ የሚኖረው ኤልሻዳዩ ፡ ጌታ ፡ ለካስ (፫x) ፡ ለካስ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ሁሉን ፡ ቻይ ፡ ጌታ ፡ ለካስ ፡ ለካስ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ይገርማል ፡ ኧረ ፡ እንዴት ፡ ይገርማል ይደንቃል ፡ ኧረ ፡ እንዴት ፡ ይደንቃል ሳልመርጠው ፡ ኢየሱስ ፡ መርጦኛል ሳልወደው ፡ እንዲህ ፡ ወዶኛል ከሞት ፡ መካከል ፡ ነጥቆ ፡ አውጥቶኛል አዝ:- ሳመሰግነው ፡ ብውል ፡ ታዲያ ፡ መች ፡ እጠግባለሁ ስዘምርለት ፡ ብውል ፡ ታዲያ ፡ መች ፡ እጠግባለሁ እልል ፡ ስልለት ፡ ብውል ፡ ታዲያ ፡ መች ፡ እጠግባለሁ ያደረገልኝን ፡ እያየሁ አምኜ ፡ በድንገት ፡ ያገኘሁት ሕይወቴን ፡ ሁሉ ፡ የሰጠሁት ይኸው ፡ እስካሁን ፡ ይመራኛል ደግሞም ፡ ዘላለም ፡ ያኖረኛል ከእጆቹ ፡ መሃል ፡ ማን ፡ ያወጣኛል ከእጁ ፡ ፈልቅቆ ፡ ማን ፡ ይወደኛል ይበልጣል ፡ ከሁሉም ፡ ይበልጣል ይመረጣል ፡ ኢየሱሴ ፡ ይመረጣል መች ፡ አሳልፎ ፡ ይሰጣል ፡ ስሙ ፡ ከስሞች ፡ ይበልጣል ኢየሱን ፡ ጠርቶ ፡ ማን ፡ አፍሮ ፡ ያውቃል አዝ:- ሳመሰግነው ፡ ብውል ፡ ታዲያ ፡ መች ፡ እጠግባለሁ ስዘምርለት ፡ ብውል ፡ ታዲያ ፡ መች ፡ እጠግባለሁ እልል ፡ ስልለት ፡ ብውል ፡ ታዲያ ፡ መች ፡ እጠግባለሁ ያደረገልኝን ፡ እያየሁ (፪x) የክብር ፡ ጌታ ፡ ድንቅ ፡ አረገ ፣ አቤት ፡ ዲያቢሎስ ፡ ተናደደ ውስጠ ፡ ሚስጥሩም ፡ ተገለጠ ፣ የጋረደውም ፡ ተቀደደ አሁን ፡ ምን ፡ ይበል ፡ ምን ፡ ይዋጠው ኢየሱስ ፡ ማንነቱን ፡ ሲገልጠው (፪x) ይነድዳል ፡ እሳቱ ፡ ይነድዳል ፣ ይዋረዳል ፡ ዲያቢሎስ ፡ ይዋረዳል መች ፡ በዚህ ፡ ብቻ ፡ ያበቃል ፣ የያዘውን ፡ ሁሉ ፡ ይለቃል ማሳወር ፡ እንጂ ፡ እሱ ፡ ማብራት ፡ የት ፡ ያውቃል ማዋረድ ፡ እንጂ ፡ እሱ ፡ ማክበር ፡ የት ፡ ይውቃል አዝ:- ሳመሰግነው ፡ ብውል ፡ ታዲያ ፡ መች ፡ እጠግባለሁ ስዘምርለት ፡ ብውል ፡ ታዲያ ፡ መች ፡ እጠግባለሁ እልል ፡ ስልለት ፡ ብውል ፡ ታዲያ ፡ መች ፡ እጠግባለሁ ያደረገልኝን ፡ እያየሁ (፪x) እስኪ ፡ እንደኔ ፡ ጌታ ፡ የሰራላችሁ በምድረ ፡ በዳ ፡ ውሃ ፡ የሰጣችሁ ይሰማ ፡ ዛሬ ፡ እልልታችሁ ፈጽሞ ፡ አይቆጠብ ፡ ድምጻችሁ (ፈጽሞ ፡ አይቆጠብ ፡ ድምጻችሁ) እስኪ ፡ እንደኔ ፡ ጌታ ፡ የሰራላችሁ በጨለማ ፡ ውስጥ ፡ ብርሃን ፡ የሆናችሁ ይሰማ ፡ ዛሬ ፡ እልልታችሁ ፈጽሞ ፡ አይቆጠብ ፡ ድምጻችሁ (ፈጽሞ ፡ አይቆጠብ ፡ ድምጻችሁ)

