Gubae

ዝናው ይወራ

Zinaw Yiwera

ሳሙኤል ተስፋሚካኤል · መልህቄ · 2022

ዝናውን ለሰማው እጅግ ያስፈራል ባለዝና እንደሱ ከየት ይገኛል በዘመናት መሃል ይታወቃል ብቻውን የበላይ ሆኖ ይኖራል እግዚአብሔር /4 እግዚአብሔርን ከእኔ ጋራ ታላቅ አርጉት ዝናው ይወራ ይወራ ዝናው ይወራ/2 በምድር ሁሉ ይወራ ይወራ ዝናው ይወራ በአለም ሁሉ ይወራ ይወራ ዝናው ይወራ አንጎዳጎደ ልኡል ቃሉን ሰጠ በክብሩ ሲቆም ምድርን አናወጠ የዘላለም ተራሮች ተፈረካከሱ የጥንትም ኮረብቶች ወዲያ ፈራረሱ ከሚንቦገቦገው ፀዳል የተነሳ ፍላፆች ከወጡበት ብርሃን የተነሳ ጨረቃ እና ፀሃይ በቦታቸው ቆሙ በክብሩ ነፀብራቅ እየተደመሙ ክብሩ ሰማያትን ሁሉ የሸፈነ ስሙም በምድር የተመሰገነ ለታላቅነቱ ፍፃሜ የሌለው በዘመናት መሃል እርጅና የማያውቀው ከዋክብት ታዘዙ በህዋ አበሩ በአፍንጫው እስትንፋስ ውሆች ተከመሩ ትልቅ የሚለው ቃል ፍፁም የማይገልፀው እጅጉን ያፈራል ዝናውን ለሰማው

ሳሙኤል ተስፋሚካኤል · ሁሉም ዘማሪዎች