Gubae

የከበረ

Yekebere

ሳሙኤል ተስፋሚካኤል · ምሳሌ የሌለህ · 2012

የከበረ ፡ ከሁሉ ፡ የተሻለ (፪x) ሰውነቴን ፡ ለአንተ ፡ አቀርባለሁ (፪x) እኔነቴን ፡ ለአንተ ፡ አቀርባለሁ (፪x) መሰዊያን ፡ ሰራሁኝ ፡ ልሰዋልህ ፡ በፊትህ ፡ ላቀርበው ያለኝን ፡ በሙሉ ፡ ታውቀዋለህ ፡ የቱን ፡ ነው ፡ ምትሻው እያልኩኝ ፡ ስደረድር ፡ ምድርና ፡ ሞላዋ ፡ ለካስ ፡ የአንተ ፡ ነው የሚቃጠል ፡ መስዋዕት ፡ ደስ ፡ እንዳያሰኝህ ፡ ይህንን ፡ ተረዳሁ ታዲያ ፡ እኔ ፡ ምኔን ፡ ልስጥህ ምኔን ፡ ሰጥቼ/ሰውቼ ፡ ደስ ፡ ላሰኝህ እያልኩኝ ፡ ስጠይቅ ፡ ቃልህን ስጠው/ሰዋው ፡ አለኝ ፡ እራስህን (፪x) ስለዚህ ፡ እራሴን ሕያውና ፡ ቅዱስ ፡ አድርጌ ፊትህን ፡ ደስ ፡ እንዳሰኘው ፈቀድኩኝ ፡ ልሰዋ ፡ ይኸው ልዩ ፡ ጣዕም ፡ የመዓዛ ፡ ሽታ ሆኜ ፡ ልቅረብ ፡ በፊትህ ፡ ጌታ ከሚቃጠል ፡ መስዋዕት ፡ ጋራ ፡ ወደፊትህ ፡ እመጣለሁ ፡ ኦሆሆ ኦሆሆ ሆሆ የአምልኮዬ ፡ መዓዛ ፡ ሽታ ፡ ዙፋንህን ፡ ይክበበው ፡ ኦሆሆ ኦሆሆ ሆሆ በምህረት ፡ የተሞላህ ፡ ታላቅ ፡ አምላክ ፡ ነህና ፡ ኦሆሆ አሁንም ፡ አበዛለሁ ፡ ከነፍሴ ፡ ምሥጋና ኦ ፡ በምሥጋና ፡ በዝማሬ ፡ እመጣለሁ ኦሆሆ ፡ ወደ ፡ ማደሪያህ ፡ እገባለሁ (፮x)

ሳሙኤል ተስፋሚካኤል · ሁሉም ዘማሪዎች