Gubae

ትለያለህ

Tileyaleh

ሳሙኤል ተስፋሚካኤል · መልህቄ · 2022

የክብር ንጉስ ሆይ እንዴት ታላቅ ነህ ከዙፋንህ ስር በእውነት በመንፈስ ልስገድልህ ከሰው ልጆች ይልቅ ያማረ ውበትህ የፀጋ ቃል ሁሌ ያፈሳል ከንፈርህ አይኖቼ አይተውህ ፈዘዙ በክብርህ /2 ማን ሊመስልህ አረ ማን ሊያክልህ አንተ እኮ ከአማልክት ትለያለህ ውዴ ከአእላፋት ትበልጣለህ ፊትህ እንደ ፀሃይ በሃይል ያበራል እንደ ብዙ ውሆች ድምፅህም ያስፈራል በግርማህ ተገረሜ ቀረሁኝ ተደምሜ ማን ሊመስልህ አረ ማን ሊያክልህ አንተ እኮ ከአማልክት ትለያለህ ውዴ ከአእላፋት ትበልጣለህ ሃሌሉያ/8

ሳሙኤል ተስፋሚካኤል · ሁሉም ዘማሪዎች