Gubae

መልካም ነህ

Melkam Neh

ሳሙኤል ተስፋሚካኤል · የሕይወት ታሪክ · 2009

እንዴት ፡ ብዬ ፡ ላመስግንህ ፡ ለእኔ ፡ ስላደረከው ፡ ሥራ ከየት ፡ ጀምሬ ፡ ልዘርዝረው ፡ ልተርከው ፡ በየተራ ኧረ ፡ እንዴት ፡ ብዬ ፡ ላመስግንህ ፡ ለእኔ ፡ ስላደረከው ፡ ሥራ ከየት ፡ ጀምሬ ፡ ልዘርዝረው ፡ ልተርከው ፡ በየተራ ቃላት ፡ ባጣ ፡ የቱን ፡ ጀምሬ ፡ እንደምጨርስ ሁለንተናዬ ፡ አንተን ፡ ያመስግን ፡ ሥራህን ፡ ያወድስ ኦ ፡ ቃላት ፡ ባጣ ፡ ከየት ፡ ጀምሬ ፡ እንደምጨርስ ሁለንተናዬ ፡ አንተን ፡ ያመስግን ፡ ሥራህን ፡ ያወድስ መልካም ፡ ነዉ ፡ እያሉ ፡ ዘመሩልህ ፡ ወንድሞቼ መልካም ፡ ነዉ ፡ ልበልህ ፡ እኔም ፡ ተስማምቼ መልካም ፡ ነዉ ፡ እያሉ ፡ አዜሙልህ ፡ ወዳጆቼ መልካም ፡ ነዉ ፡ ልበልህ ፡ እኔም ፡ ተስማምቼ ለእኔ ፡ መልካም ፡ በማድረግ ፡ የታወቀው (፪x) ለእኔ ፡ መልካም ፡ በማሰብ ፡ የታወቀው (፪x) ሰው ፡ ሁሉ ፡ ያውቀዋል ከአንተ ፡ በላይ ፡ መልካም ፡ የሚያደርግልኝ ፡ እንደሌለ ሀገር ፡ ሁሉ ፡ ያውቀዋል ከአንተ ፡ በላይ ፡ መልካም ፡ የሚያደርግልኝ ፡ እንደሌለ ሁልጊዜ ፡ ለእኔ ፡ መልካም ፡ ነህ (፫x) በእናቴ ፡ ማህፀን ፡ ሳለሁ ፡ አጥንቶቼም ፡ ሳይዋደዱ ደፋ ፡ ቀና ፡ ስል ፡ አድጌ ፡ እግሮቼም ፡ ቆመው ፡ ሲሄዱ (፪x) ሳልፈጠር ፡ የተፈጠሩ ፡ ቀኖቼን ፡ ያየህ መልካም ፡ እየሆንክ ፡ እስከ ፡ ዛሬ ፡ እኔን ፡ እረዳህ (፪x) መልካም ፡ ነዉ ፡ እያሉ ፡ ዘመሩልህ ፡ ወንድሞቼ መልካም ፡ ነዉ ፡ ልበልህ ፡ እኔም ፡ ተስማምቼ መልካም ፡ ነዉ ፡ እያሉ ፡ አዜሙልህ ፡ ወዳጆቼ መልካም ፡ ነዉ ፡ አየሁህ ፡ እኔም ፡ በሕይወቴ ለእኔ ፡ መልካም ፡ በማድረግ ፡ የታወቀው (፪x) ለእኔ ፡ መልካም ፡ በማሰብ ፡ የታወቀው (፪x) ሰው ፡ ሁሉ ፡ ያውቀዋል ከአንተ ፡ በላይ ፡ መልካም ፡ የሚያደርግልኝ ፡ እንደሌለ የሚያውቀኝ ፡ ያውቀዋል ከአንተ ፡ በላይ ፡ መልካም ፡ የሚያደርግልኝ ፡ እንደሌለ ሁልጊዜ ፡ ለእኔ ፡ መልካም ፡ ነህ (፫x) ተመስገን ፡ ተመስገን ተመስገን ፡ የእኔ ፡ ጌታ ተመስገን ፡ ልበልህ ተመስገን ፡ ለዘለዓለም ተመስገን (፪x)

ሳሙኤል ተስፋሚካኤል · ሁሉም ዘማሪዎች