በመድህኔ
Bemedine
ሳሙኤል ተስፋሚካኤል · መልህቄ · 2022
በእኔ ፈንታ ተተክቶ ወጥቻለው እስሬ ተፈቶ በሃጥያቴ ምክንያት እንዳልቀጣ ክርስቶስ እየሱስ ክብሩን ትቶ መጣ እዳዬንም እሱ ከፍሎልኛል ነፃ ሰው ነኝ ዋሴ ሆኖልኛል አድራሻዬ በሰማዩ ስፍራ አድርጎታል ከእግዚአብሔር ጋራ ኩነኔ የለብኝም አሁን ኩነኔ ነፃ ወጥቻለው በመድህኔ ምንም ሳላደርግ ምንም ሳልስራ በአብ ቀኝ ተቀመጥኩ ከእየሱሴ ጋራ ምንም ሳልከፍል ያለምንም ዋጋ የዘላለም ህይወት አገኘው በፀጋ እንዲሁ በፀጋ/2 የዘላለም ህይወት አገኘው በፀጋ ራሱ ሰጠ ለኔ ሊገረፍ አንድም ጅራፍ በኔ ላይ እንዳያርፍ መራራውን ፅዋ እንዳልጠጣው አበሳዬ ወስዶ ጨረሰው የአለምን ሃጥያት ሚያስወግደው የእግዚአብሔር በግ በደሌን ሰቀለው በራሱ ደም ይዞኝ አብ ጋር ገባ አለበሰኝ ፀጋውን እንደ ካባ

