Gubae

Tiwus Diken

ሳምራዊት ሲዛር · Yene Aleme

ትውስ ፡ ድቅን ፡ ይልብኛል ፡ አይኔ ፡ ላይ እየሱሴ ፡ መስቀሉ ፡ ላይ የተወጋው ፡ ጎኑ ፡ ደሙ ፡ የፈሰሰው እኔን ፡ ከሃጥያቴ ፡ ሊያጥበኝ ፡ ነው የቆሰለም ፡ ጀርባው ፡ የተገረፈው እኔን ፡ ከእግዚአብሔር ፡ ጋር ፡ ሊያስታርቀኝ ፡ ነው እንዴት ፡ ነው ፡ የምትወደኝ/3 ምህረትህ ፡ ሰው ፡ አረገኝ ደምህ ፡ ሲፈስልኝ ፡ በቀራንዮ ፡ ላይ እርግማኔን ፡ ስትወስድ ፡ ስትሞት ፡ መስቀል ፡ ላይ ያን ፡ ሁሉ ፡ አበሳ ፡ ለኔ ፡ ነው ፡ ለኔ ፡ ነው ማንም ፡ አላስገደደህ ፡ ፍቅር ፡ ይዞህ ፡ ነው/2 ፍቅርህ ፡ ያንተን ፡ ፍቅር ፡ እየሱስ የትም ፡ አላየሁት ፡ ማንም ፡ ላይ ፡ አላየሁት ልዩ ፡ ነው ፡ ፍቅርህ/4 ባነበብኩት ፡ ብቻ ፡ አይደለም በሰማሁት ፡ ብቻ ፡ አይደለም ምህረትህ ፡ እየተከተለኝ ስቀድቅ ፡ እርሱ ፡ አይደለም ፡ ወይ ፡ የሚያነሳኝ ስደክም ፡ የሚያቆመኝ አንተ ፡ መልካም ፡ አንተ ፡ መልካም ፡ ነህ ኧረ ፡ አንተ ፡ መልካም ፡ አንተ ፡ መልካም ፡ ነህ መልካም ፡ ነህ ፡ መልካም ፡ ነህ አንተ ፡ መልካም ፡ ነህ ክበርልኝ ፡ አንተ ፡ የኔ ፡ ጌታ ክበርልኝ ፡ አንተ ፡ የኔ ፡ ወዳጅ/4 ትውስ ፡ ድቅን ፡ ይልብኛል ፡ አይኔ ፡ ላይ እየሱሴ ፡ መስቀሉ ፡ ላይ የተወጋው ፡ ጎኑ ፡ ደሙ ፡ የፈሰሰው እኔን ፡ ከሃጥያቴ ፡ ሊያጥበኝ ፡ ነው የቆሰለም ፡ ጀርባው ፡ የተገረፈው እኔን ፡ ከእግዚአብሔር ፡ ጋር ፡ ሊያስታርቀኝ ፡ ነው እንዴት ፡ ነው ፡ የምትወደኝ/3 ምህረትህ ፡ ሰው ፡ አረገኝ

ሳምራዊት ሲዛር · ሁሉም ዘማሪዎች