ቃልህ
Qaleh
ሳምራዊት ሲዛር · Yene Aleme
አፀናኸ ፡ ልቤን ፡ ምንም ፡ እንዳይሆን በፈተና ፡ ጎርፍ ፡ እንዳይወሰድ ንፋሱ ፡ ነፍሶ ፡ ዝናቡም ፡ ዘንቦ ህይወቴን ፡ ቤቴን ፡ አላፈረሰውም ያምላኬ ፡ ቃሉ ፡ ልቦና ፡ ሰቶኝ ቤቴን ፡ ባለት ፡ ላይ ፡ አይደል ፡ ወይ ፡ ያሰራኝ የተዘራውን ፡ ቃል ፡ አልበሉትም ፡ ወፎች የሰማሁትን ፡ ቃል ፡ አልያዘውም ፡ እሾህ በመንፈስ ፡ ታርሶ ፡ ነው ፡ የገባው ፡ ልቤ ፡ ውስጥ በውሃ ፡ ዳር ፡ እንዳለ ፡ ዘፍ ፡ ፍሬው ፡ አይቋረጥ በወንዝ ፡ ዳር ፡ እንዳለ ፡ ዘፍ ፡ ፍሬው ፡ አይቋረጥ ቃልህ ፡ ይይዘኛል/4 ደክሜ ፡ እንዳልጠፋ ፡ ቃልህ ፡ ይይዘኛል/2 ደክሜ ፡ እንዳልጠፋ ፡ ቃልህ ፡ ይይዘኛል/2 በእጄ ፡ ቃል ፡ አለ ፡ በእጄ ፡ ላይ/3 አሸናፊ ፡ አረገኝ ፡ የበላይ መልካም ፡ እድል ፡ የማይወሰድ ከእግርስ ፡ በታች ፡ ጌታ ፡ መሆን መልካም ፡ እድል ፡ የማይወሰድ ከእግሮችህ ፡ ስር ፡ ሆና ፡ ቃልህን ፡ መማር ይሁንልኝ ፡ ይሁንልኝ የኔ ፡ አባት ፡ አንተው ፡ ምራኝ ፡ አስተምረኝ/2 ኦ ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ አንተ ፡ አውራኝ ፡ አስተምረኝ/2 ይሁንልኝ ፡ ይሁንልኝ የኔ ፡ አባት ፡ አንተው ፡ ምራኝ/2 መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ አንተ ፡ አውራኝ ፡ አነጋግረኝ ፡ አስተምረኝ

